• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን  

October 6, 2024 03:20 pm by Editor Leave a Comment

“ዝምታ ነው መልሴ” ሲሉ ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ድምጻቸውን በቲውተር በኩል በዘፈን ምርጫ አጅበው ብቅ ያሉት ለስንብት ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነው። “የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው” ሲሉ የተቀኙት ፕሬዚዳንቷ “ለአንድ ዓመት ሞከርኩት” በሚል ሐረግ መልዕክታቸውን አስረውታል።

ይህኔ ነው “የኔታ መስፍን ወልደማርያምን ነብሳቸውን ይማረው” ሲሉ ፋይል ያገላበጡ ፕሬዚዳንቷ በኤክስ ይፋዊ ገጻቸው ላይ ላሰፈሩት ቅኔ ምላሽ የሰጡት። አንዳንዶች “ክብርት ሆይ ሕዝብም መንግሥትም መሆን አይቻልም” ሲሉ ቀልደውባቸዋል።

ግልጹ፣ ያመኑበትን ለመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ የአደባባዩ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን “ለሦስት መንግሥት ያገለገለች” ሲሉ በሎሌነት የመሰሏቸው የሳህለወርቅ ዘውዴን ሹመት በፍጹም እንደማይቀበሉት ተናግረው ነበር።

ለስንብት ሁለት ቀን ሲቀር እንጉርጉሮ የመረጡት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የተቀመጡበት ወንበር ለመሆኑ “ዝምታ ነው መልሴ፣ አንድ ዓመት ቻልኩት” ያሰኛል? መለስ ዜናዊ ለክቶና መትሮ ያረቀቀው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሥልጣን ለግንዛቤ እንዲሆን በሚል በርካቶች “ዳግም አስተውሉ። ዝም ብላችሁ አትንጎዱ” ሲሉ ከሕገ መንግሥቱ ጠቅሰዋል።

አንቀጽ 71 የኘሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር በሚል ርዕስ በዝርዝር እንደሚከተለው የደነገገው የኃላፊነት ዕርከን ሳህለወርቅ እንዲያጉረመርሙ፣ በአሽሙር እንዲቀኙ፣ ዘፈን እንዲመርጡ ያስችላል? ሞት የወሰደው መለስ ያኖረላቸው ሥልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት ከታች ያለው ነው፤

1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል።
2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሠረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለምአቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጀል።
3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል።
4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል።
5. በሕግ መሠረት ኒሻኖች እና ሽልማቶችን ይሰጣል።
6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሠረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል።
7. በሕግ መሠረት ይቅርታ ያደርጋል።

እንግዲህ ይህ ከሆነ ከተዘረዘሩት ሰባት ኃላፊነት የቱን ነው እንዳያከናውኑ የተከለከሉት? በሚል መጠየቅ ግድ ይላል። በሰበር ታጅቦ፣ አስቀድሞ አልቅሶ ለማልቀስ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አዛኝ፣ አልቃሽ፣ ልቡ የተሰበረ፣ መሄጃ የሌለው፣ የተገፋ፣ ወዘተ መስለው የቀረቡት ሊሰናበቱ ቀናት የቀራቸው ፕሬዚዳንት እንግዳ እንዳይቀበሉ ተከልክለው ያውቃሉ? ወይስ በፓርላማ የጸደቀ ሕግ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሄደው እንዳያሳትሙ ታገዱ? ወይስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቡትን ሹመት እንዳያጸድቁ ተከለከሉ? ኒሻን አትስጡ ተባሉ? ይቅርታ አያድርጉ ተባሉ? ወይስ ለቅሶ ለመድረስ ወደ ውጭ አገር አይሂዱ ተብለው ተከልክለዋል? መለስ ሰፍሮ ካሰቀመጠላቸው የትኛውን ሥልጣናቸውን ተከልክለው ነው ባለቀ ሰዓት አሽሙር የመረጡት?  

በተሰናባቿ ፕሬዚዳንት ሹመት ማግስት በግራም በቀኝም ያለው ሁሉ ልምድ ያላቸውና ለቦታው ብቁ የሆኑ በሚል አድናቆቱን ለሳህለወርቅና ለሾማቸውም ክፍል እንደ ጉድ በሚጎያጎርፍበት ወቅት አፈሩ ይቅለላቸውና የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም በድፍረት “አድሮ ይታያል” ብለው ነበር። ይህንንም ያሉት በተለይ በዲፕሎማሲው መስመር ለወያኔ የሰጡትን አገልግሎት በመጥቀስ እንደሆነ ይታወሳል።

Meles Zenawi arrives escorted by United Nations Office in Nairobi Director General, Sahle-Work Zewde on September 9, 2011 to a Horn of Africa drought crisis summit in the Kenyan capital Nairobi (Photo credit should read TONY KARUMBA/AFP via Getty Images)

ፕሬዚዳንቷ የኢትዮጵያ ሕዝብ “አልበተንም” ብሎ የኅልውና ጦርነት ሲያካሂድ አቋማቸው ልክ እንዳልነበረ ማስታወስ ግድ ይላል። መሪዋ ጦር ሜዳ ሲዘምት የዲፕሎማሲውን ኮሪደርና መሿለኪያ አሳልጦ ከሚያውቅ ሰው በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያ ምን ተጠቀመች? ምንስ መጠቀም እየቻለች አመለጣት? አገራችን በዓለምአቀፉ መድረክ ስትብጠለጠል ሊደረግላት የሚገባ ግን የቀረባትስ ምንድነው? ብሎ በመጠየቅና የፕሬዚዳንቷ አቋም መከለስ ተገቢ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ወ/ሮ ሳህለወርቅ በወቅቱ አልፎ አልፎም “አገም ጠቅም” የሚባል ዓይነት አቋም ሲያራምዱ የታዘቡ እነዚሁ ወገኖች “ሰሞኑን ስድስተኛ ዓመታቸውን ከጨረሱ የሚቀጥሉ አይመስልም” ሲሉ ቀድመው አስታውቀዋል። እናስ ምኑ ነው የርሳቸውን መሰናበት ሰበር የሚያደርገው? 

“ዝምታ ነው መልሴ የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው፤ ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፤ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው፤ ለአንድ ዓመት ሞከርኩ” ያሉት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ፣ ከላይ ትህነግ ባወጣው ሕግ መሠረት ይህን መዝፈናቸው ቤተ መንግሥት ቁጭ ብለው ዘፈን እያዳመጡ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ከማስታወቁ በስተቀር ሌላ ፋይዳ እንደሌለው በስፋት አስተያየት ተሰጥቷል።

በሌለ ሥልጣን ምሬትና ለቅሶ አይለቀስም፤ ጨዋነትም አይደለም። ልክ ታዬ ደንደአ እንዳደረጉት ዓይነት መሆን ነው። አቶ ታዬ ደንደአ ከሥልጣን ሲሰናበቱ “ተሸውጃለሁ” በሚል በቲውተር ገጻቸው ላይ በአማርኛና ኦሮምኛ የጻፉት ጽሑፍ ልክ እንደዛሬው የሳህለ ወርቅ “የዘፈን ቅኔ” ሰበር የሚል ታርጋ ተለጥፎለት ሲሰራጭ ነበር። አቶ ታዬ ጥፋተኛ ይሁኑ አይሁኑ ለጊዜው ብዙ ማለት ቢያስቸግርም ከስልጣን ሲነሱ “ተሸውጄ ተከትዬሃለሁ፣ ተድምሪያለሁ” ማለታቸው አስተችቷቸው ነበር። ምክንያቱም ስልጣን “በቃዎት” ሲባሉ በመሆኑ ነው።

በደፈናው በቅኔና በሙሾ መልክ የቀረበው የወይዘሮ ሳህለወርቅ የግጥምና የዜማ ጽሑፍ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ፤ ምን ለመናገር ታስቦ እንደሆነ በሰኞው የስንበት ንግግራቸው የተሰጣቸውን ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው እንዲያብራሩ ይጠበቃል። ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጪ ማብራሪያ ካቀረቡ “በፕሬዚዳንት ደረጃ የቀረበ አሽሙር” ተብሎ ለትውልድ መማሪያ ይሆናል። ምክር ቤቱም ሕጉን እያነበበ “ክብርት ሆይ! ምን ጎደለብዎት?” ብሎ ሊጠይቃቸው ግድ ነው። በሕግ ከተቀመጠው ውጪ የተሰማ የመጨረሻ ለቅሶ ከሆነ እንደ አዜብ መስፍን “ቤተ መንግሥቱን እስክሞት ልኑርበት” ማለት ይሆናልና ምን አልባትም የጡረታና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ሊያሳጣ ይችላል የሚል ስጋትም እየተሰማ ነው።

አንዳንዶች “አሁን ባለው ስርዓት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነው እየሠሩ ያሉት፤ በተለያዩ ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥም እንደነበሩ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ይሰማ ነበር፤ ለመናገር እንኳን ዕድል የላቸውም፤ ባገኙት አጋጣሚ ግን በገደምዳሜው ስሜታቸውን ስለ ሀገራቸው ይናገሩ ነበር፤ አሁንም ቦታውን ሲለቁ ስለዚህ ስርዓት ብዙ የሚናገሩት ይኖር ይሆናል” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

“በዚህ ልክ ትልቅ የሥልጣን እርከን ይዘው ሕዝብን ግራ የሚያጋባ ድፍንፍን ያለ ጽሑፍ በገጻቸው መጋራቱ ሳያንስ እውነትም እርሳቸው መሆናቸውን በግልጽ አለማብራራታቸው ትክክል አይደለም፤ ችግር ካለም እውነታውን ለሕዝብ ማሳወቅ አለባቸው፤ እንዲህ የዘፈን ግጥም ከሚያስቀምጡ” በሚል አንዳንዶች አስተያየት እንደሰጡት ቲክቫህ ጽፏል።

በዚሁ ሚዲያ የተጠቀሱ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ “የ6 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ ይህን ዓይነት ነገር በገጻቸው መጻፋቸው የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት ነው። እስከዛሬ በሀገሪቱ ብዙ ነገር፣ ብዙ ግፍ ሲፈጠር ባላየ ሲያልፉ ነበር። አንዳንዱን ደግሞ እየመረጡ ሲናገሩ ነበር። ለምን አሁን? በዚህ ሥልጣን እንደማይቀጥሉ ስለሚያውቁ ነው? ሥልጣንም መልቀቅ ከነበረባቸው ቀድሞ ተናግሮ እንጂ አሁን ላይ ይህን አጀንዳ ለሕዝብ መስጠት ትክክል አይደለም። ጊዜያቸው አብቅቷል ይሰናበታሉ። እሱንም ስለሚያውቁ ነው” ሲሉ ጽፈዋል።

በኢትዮጵያ የፕሬዚዳንት ሥልጣን ዘመን 6 ዓመት ሲሆን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ወደ ሥልጣን የመጡት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ላይ ነበር።

በገለልተኛነታቸው የሚታወቁ አስተያየት ሰጪዎች፣ የተሰጣቸውን ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን እየጠቀሱ የተበደሉትን በአመክንዮ ማስረዳት ስለመቻላቸው አስቀድሞ ማረጋገጥ ሳይቻል ብዙ ማለት አስፈላጊ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የሚባለው ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ሥልጣንና ተግባርን አስመልክቶ ይደነግጋል። በምዕራፍ ሰባት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በአንቀጽ 69 የቀረበው “ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው” ይላል።

አንቀጽ 70 የፕሬዜዳንቱ አሰያየም አስመልክቶ፤
1. ለፕሬዚዳንትነት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
2. የቀረበው ዕጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዚዳንት ይሆናል።
3. የምክር ቤት አባል ፕሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል።
4. የፕሬዚዳንቱ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ነው። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዚዳንትነት ሊመረጥ አይችልም፤ ይላል።

በዚህ ስሌት መሠረት ሳህለወርቅን ፕሬዚዳንት አድርጎ የሾማቸውና ያቀረባቸው ይህ መድረክ ሰኞ ወደ ወይዘሮነት ሊመልሳቸው ይችላል፤ ይህ መብቱ ነው። በግልጽ በሕግ የተቀመጠ ነው። ሕገ መንግሥቱ እስኪቀየር ይህ ይቀጥላል። ምናልባት በጋራ ምክርቤቱ “ከመባረራቸው” በፊት አስቀድመው የሥልጣን መልቀቂያ ወይም ድጋሚ መመረጥ አልፈልግም ብለው ሊያሳውቁ ይችላሉ። እንደ ሰበብ ግን የዘፈን እንጉርገሯቸውን አሰምተዋል፤ ይህ ደግሞ በፖለቲከኞች ዘንድ ተገማች ነው።

አቶ ሀይደር  መሐመድ “የወይዘሮ ሳህለወርቅ ለቅሶ አላማረኝም” በሚል በማኅበራዊ ገጻቸው ይህን ጽፈዋል፤ “ባለ ቀይ መስመሯ እናታችን ከቢሯቸው ወጥተው መቶ ሜትር ቢራመዱ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር በግላጭ ማግኘት ይችላሉ። ስልካቸውን አውጥተው ቁጥር ቢመቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሃሎ” ይሏቸዋል። ነገር ግን እናታችን ብሶታቸውን እንደ አክቲቪሲት ትዊተር ላይ ነው የሚገልጹት።

“በዚያ ላይ አንድ ዓመት የታገሱ ሴት አንድ ቀን መታገስ አቅቷቸው በዕለተ “ኢሬቻ” መናገርን መረጡ። ከ 365 ቀን የመሃሙድ አህመድ ዘፈን ትዝ ያላቸው በዕለተ ኢሬቻ ነው።

“የተከበሩ ታዬ አጽቀሥላሴ የሆነ ስብሰባ ላይ “መንግሥታት እንደ አክቲቪስት መሆን የለባቸውም” ብለው የሱማሊያን መሪዎች ሸንቆጥ አድርገው ነበር። እንደው “የራስ እንትን አይሸትም” እንጂ የኛም መሪዎች አክቲቪስት እየሆኑ ነው የተቸገርነው።

“የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዳንኤል ክብረትን አንዱ ጋዜጠኛ “ድሮ መንግሥትን ትተች ነበር አሁን ለምን አቆምህ?” ሲለው “አሁንማ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለራሱ እነግረዋለሁ” ብሎ ነበር።

“ፕሬዚዳንትም እንደ ሕዝብ “ተው ልመድ ገላዬ” እያለ ካንጎራጎረማ አራት ኪሎ መቀመጡ ለምን አስፈለገ ታዲያ? እኚህን ስንዱ እመቤት የማግኘት ዕድሉ ቢኖረኝ በተመሳሳይ ሰዓት ሕዝብም መንግሥትም መሆን እንደማይቻል እነግራቸው ነበር” ሲሉ ሀይደር መሐመድ በምኞት ያበቃሉ።

ወይዘሮ ሳህለወርቅ በደርግና በኢህአዴግ ዘመን በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት/ በዲፕሎማትነት አገልግለዋል። በተለይ በትህነግ (በወያኔ) የግፍ ዘመናት በአፍሪካና በተባበሩት መንግሥታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ሆነው ሠርተዋል። እ.ኤ.አ. በ2011 የመንግሥታቱ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ሳህለወርቅን በናይሮቢ (UNON) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾመዋቸው ነበር። በዚህ ሹመታቸው ወቅት እሳቸው የተቀመጡበት የናይሮቢው ጽሕፈት ቤት በ2012 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋና ማዕከል መሆኑ ይታወሳል።

እ.ኤ.አ ሰኔ 2018 ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሳህለ ወርቅን በአፍሪካ ኅብረት ልዩ ወኪላቸውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት ጽሕፈት ቤት (UNOAU) ኃላፊ አድርገው ትልቅ ሹመት ሰጥተዋቸዋል። ለዚህ ሹመት ሲበቁ በቦታው ላይ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። ሳህለ ወርቅ ጡረታ ለመውጣት እየተዘጋጁ ነበር ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ይህን ሥልጣን ቢያገኙም ምንም ሳይቆዩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ከብልጽግና መንግሥት ጋር መሥራታቸውን ተከትሎ ለሦስት መንግሥታት ያገለገሉ ሰው መሆናቸውን ጠቅሰው የተቃወሙት ፕሮፌሰር መስፍን መከራከሪያቸው እሳቸው በዓለም ዓቀፍ መድረክ በነበራቸው ኃላፊነት ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ለሰላሳ ዓመት ያህል በዚያ ደረጃ ሲረግጥና ሲጨፈጭፍ ሳህለ ወርቅ ድጋፍ ይሰጡና ሥርዓቱን በታማኝነት ያገለግሉ እንደነበር በመናገር ነው። የውጭ አካላትና ታላላቅ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ወያኔን እንዳይቃወሙ እርሳቸው አበክረው ይሠሩ እንደነበር ጠቅሰው ነው ሎሌ ነች ለቦታው አትመጥንም ሲሉ የሞገቱት።

ይፋ ባይሆንም ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በፕሬዚዳንትነት ወንበራቸው ላይ ሆነው ከትህነግ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅት ካገኟቸው የውጭ አካላት ጋር በትክክል መንግሥት የያዘውን አቋም ስለማራመዳቸው ጥርጣሬ ያላቸው፣ መንግሥት ሆዱ የቆረጠው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይናገራሉ።

እጅግ ፌሚኒስት እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት ስለሆኑ ሰንዳፋ ባለ ማዕከል ለአዳዲስ ዲፕሎማቶች ልማዳቸውን ሲያካፍሉ ከኢትዮጵያውያን እሴቶች ጋር የማይገጥሙና ከነጮጩቹ በውሰት የተቀዱ “ዕውቀቶችን” መናገር ሲጀመሩ ስብሰባው ላይ የተገኙ ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ ባለሥልጣን “ይህ የሥልጠናው አካል አይደለም አቁሚ” ብለው እንዳስቆሟቸው የሚያስታውሱ፣ ፕሬዚዳንቷ ኮንትራታቸው እንደማይታደስ፣ በሥልጣን እንደማይቀጥሉ አስቀድመው እንዳወቁ አመልክተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: abiy ahmed, president of ethiopia, sahle work, sahlework, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule