"ዝምታ ነው መልሴ" ሲሉ ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ድምጻቸውን በቲውተር በኩል በዘፈን ምርጫ አጅበው ብቅ ያሉት ለስንብት ሁለት ቀናት ሲቀራቸው ነው። "የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው፣ መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው" ሲሉ የተቀኙት ፕሬዚዳንቷ "ለአንድ ዓመት ሞከርኩት" በሚል ሐረግ መልዕክታቸውን አስረውታል። ይህኔ ነው "የኔታ መስፍን ወልደማርያምን ነብሳቸውን ይማረው" ሲሉ ፋይል ያገላበጡ ፕሬዚዳንቷ በኤክስ ይፋዊ ገጻቸው ላይ ላሰፈሩት ቅኔ ምላሽ የሰጡት። አንዳንዶች "ክብርት ሆይ ሕዝብም መንግሥትም መሆን አይቻልም" ሲሉ ቀልደውባቸዋል። ግልጹ፣ ያመኑበትን ለመናገር ወደኋላ የማይሉት፣ የአደባባዩ ምሑር ፕሮፌሰር መስፍን "ለሦስት መንግሥት ያገለገለች" ሲሉ በሎሌነት የመሰሏቸው የሳህለወርቅ ዘውዴን ሹመት በፍጹም እንደማይቀበሉት ተናግረው … [Read more...] about የሦስት መንግሥታት “ሎሌ” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ”ሳልቀደም ልቅደም” የስንብት ዘፈን