በአንድ ጊዜ 8ሺ ሰው በአንድ ቀን ደግሞ እስከ 40ሺ ሰው የሚስተናገድበት ትልቅ የድግስ አዳራሽ በአዲስ አበባ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከ120 አመት በፊት ሲሠራ የነበረው የምህንድስና፣ ቅርጽና ይዘት፣ የመንግሥታዊ ድግሡ ታዳሚዎች ማንነትና የግብሩ ሥርአት፣ “ቀድሞም ጠቢብ ነበር ሰለሞን አባቱምኒልክ ይበልጣል ሰው ይዞ መብላቱ” ዳግማዊ ምኒልክ ሰዉ ሁሉ አንድ ጊዜ ተሰብስቦ የሚበላበትን ትልቅ አዳራሽ ለመስራት በመወሰን፣ በ1889 ዓ.ም ክረምቱን መናገሻ ወርደው እንጨት ሲያስጠርቡ ከረሙ፡፡ ወታደሩም በድግስ ጊዜ ሜዳ ላይ ሆነን ጸሀይና ዝናብ እንዳይመታን ለኛ ብለው አይደለምን በማለት ደስ ተሰኘ፡፡ ላዳራሹ የሚያስፈልገውን 4 ማዕዘን፣ ሳንቃና እንጨትም ላሊ እየወጣና እየዘፈነ ማመላለስ ጀመረ፡፡ በ1890 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ዳግማዊ ምኒልክ ከአውሮፓ መሀንዲሶችን … [Read more...] about የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ