ሁሉም ባይባልም አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና የፖለቲካ ፕሮግራም ሶሻል ዴሞክራሲ ወይም ሊበራል ዴሞክራሲ ወይም ምርጫን ማዕከሉ ያደረገ ዴሞክራሲያዊ ፖሊሲ ነው። የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ደግሞ ገበያ መር ኢኮኖሚ ነው። እነዚሁ ፓርቲዎች በምርጫ ክርክር ሲደረግ በዋናነት እያነሱ የሚከራከሩት መንግሥት ኢኮኖሚውን ተቆጣጥሮታል፤ የዕዝ ኢኮኖሚ ነው አገሪቱን ለችግር የዳረጋት፣ የኢኮኖሚው አካሄድ በገበያ እንጂ በመንግሥት መመራት የለበትም በሚል የከረረ ተቃውሞ በማቅረብ ሲቃወሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰምተናል። ባለፈው ሰኞ መንግሥት የአገሪቱን ዐቢይ (ማክሮ) ኢኮኖሚ ወደ ገበያ መር የሚወስድ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ እነዚሁ ተቃዋሚዎች “እሰይ ስለቴ ሰመረ” ባይሉም ቢያንስ ለዓመታት ሲሟገቱለት የነበረው ሃሳብ ድል አድርጎ በማየታቸው ጥንቃቄ የተሞላበት ድጋፍ ሊያሰሙ የሚጠበቅ … [Read more...] about “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አእምሮና የደም ዝውውር ሊኖረው ነው”
Politics
“እንደ ጌታቸው ዐቢይን አልተሳደብኩም፤ ለምን ሥልጣን ከለከሉኝ?” ደብረጽዮን
ጌታቸው ረዳ በድምጸ ወያኔ በርካታ ምሥጢር ይፋ አድርገዋል፤ ወደ ሚዲያ የወጣበት አንዱ ምክንያት “በስብሰባ ላይ መናገር ስላልቻልሁ” ነው በማለት ተናግሯል። ደብረጽዮንን ጨምሮ የተለያዩ የትህነግ አመራሮችም ሆኑ የወታደር አዛዦች የፕሪቶሪያውን ስምምነት “ባክህን አድነን ፈርም፤ አለበለዚያ ወደ ቆላ ተምቤን ልንሄድ ነው” እያሉ ይገፉት እንደነበር ገልጾዋል። እነ ደብረጽዮን ይህን ባደረጉ ማግስት “ከጀግና ወደ ባንዳ ወደ ይሁዳ” እንዳወረዱትም ጌታቸው በግልጽ አመልክቷል። የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ደብረጽዮን በየቦታው እየዞረ “በቅልጥማችን ወይም በጉልበታችን ፌዴራል መንግሥትን ወደ ጠረጴዛ አመጣነው” ሲል ተደምጧል። በነጻ ሚዲያ ላይ ከስዩም ተሾመ ጋር ውይይት ያደረገው አርአያ ተስፋማርያም ሌላ የሰጠው መረጃ አለ፤ “በ3ኛው ዙር መከላከያ መቀሌ ሊገባ ሲል እየገሰገሰ ሳለ … [Read more...] about “እንደ ጌታቸው ዐቢይን አልተሳደብኩም፤ ለምን ሥልጣን ከለከሉኝ?” ደብረጽዮን
ኢትዮጵያ 16.6 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ አገኘች
ለሁለት ዓመታት የተደረገው ድርድር ያስገኘው ውጤት ነው የዓለም ባንክ በዛሬው ዕለት (ማክሰኞ) “የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘላቂና ሁሉን ዓቀፍ የልማት ፖሊሲ ዘመቻ” (Ethiopia First Sustainable and Inclusive Growth Development Policy Operation) በሚል ለሚጠራው የልማት ፖሊሲ ማስፈጸሚያ የሚሆን ድጋፍና ብድር መፍቀዱን ይፋ አድርጓል።በወጣው መግለጫ መሠረት ባንኩ የሚያደርገው ድጋፍ ሦስት ዓላማዎችን ያካተተ ነው፤ (ሀ) ለመዋቅር መልሶ ማዋቀርና ንግድን ለማሳለጥ (ለ) በጀትን በተመለከተ ዘላቂነትንና ግልጽነትን ለማስፋፋት እና (ሐ) የአካባቢ ጥበቃን እና ማኅበራዊ አይበገሬነትን ለማበረታታት እንደሆነ ተገልጾዋል። በተለምዶ የዓለም ባንክ የሚባለው ቡድን ሲሆን በሥሩም የተለያዩ ድርጅቶች አሉት፤ ብድርም ሆነ ሥጦታ ሲፈቀድ … [Read more...] about ኢትዮጵያ 16.6 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ አገኘች
በእስክንድርና በዘመነ ሽኩቻ ፋኖ አንድ መሆን የማይችል ሆኗል – ኮሎኔል አሰግድ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰግድ መኮንን እጁን ሰጠ በአማራ ክልል በርካታ የታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግሥት የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ሰላማዊ ሕይወት እየመሩ መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይሉ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩትን የፀጥታ ችግሮች በንግግርና በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በመንግሥት ለታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በተደጋጋሚ የሰላም አማራጮች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና በክልሎችም ሆነ በፌዴራል መንግሥት እየቀረበ ያለው የሰላም አማራጭ እንዳይሳካ እና ወደ መሬት እንዳይወርድ በተለይም ደግሞ ውጭ ሆነው በትግሉ ስም ጥቅም የሚያግበሰብሱ አንዳንድ ጽንፈኛ … [Read more...] about በእስክንድርና በዘመነ ሽኩቻ ፋኖ አንድ መሆን የማይችል ሆኗል – ኮሎኔል አሰግድ
ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር እየሮጠ ነው
ገና ከጅምሩ “አንደ ወጥ አመራር፣ ድርጅታዊ ግብ፣ ዓላማ የለውም፤ በዚህ አካሄድ ጦርነት ማካሄድ ይከብዳል፤ ጊዜያዊ ድሎች ቢመዘገቡም ዘላቂ ድል ማግኘት ያስቸግራል” የሚለው በአማራ ክልል የተነሳውን ግጭት አስመልክቶ በስፋትና በተደጋጋሚ ሲስጥ የቆየ አስተያየት ነው። ይህ መሠረታዊ ሐቅ የገባቸው አንድ ለመሆን ብዙ የጣሩ ሲሆን፤ በርካታዎች ግን በተለይ በውጭ አገር በሚላክላቸው ዳረጎት “ፋኖ” የሚል ስም ይዘው በሕዝባቸው ላይ ብረት ያነሱ በመሆናቸው የአንድነት ጉዳይ ብዙም የሚመቻቸው ሳይሆን ቆይቷል። የስምምነት ውይይቶችም ሊደረጉ ሲሉ ከአረብ አገር እስከ አውሮጳና አሜሪካ እንደ ግል ካምፓኒ (ፒኤልሲ) የተዋጊ “የፋኖ” ሱቅ የከፈቱት ዳያስፖራዎች “ቧንቧውን እዘጋዋለሁ” እያሉ በማስፈራራት ተፈላጊው አንድነት እውን ሳይሆን ቀርቷል። በመንግሥት በኩል “አንድ ሁኑ እና እንደራደር” … [Read more...] about ዘመነ ካሤ ቀድሞ ወደ ድርድር እየሮጠ ነው
የኅቡዕ ቡድን ሪፖርት በኅቡዕ በሚሠሩ “ኢትዮጵያውያን” – ኢትዮጵያ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ!
የስሙ መነሻ ግንድ የሚመዘዘው ከላቲን ነው። “vates” ይባላል። ትርጉሙም “prophet” ነቢይ፣ ወይም Fortune teller ትንቢት አብሳሪ፣ የወደፊቱን ገላጭ እንደ ማለት ነው። ስሙንም ስያሜውንም ጠቅሶ ማብራሪያ ያኖረው ራሱ ቡድኑ ሲሆን ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው “ሰማያዊ ቅባትን” ራሱ ላይ ደፍቷል። የአደባባይ የድረገጹ ስምና መገኛው vatescorp.com ነው። ምርመራና የሥጋት ቅድመ ትንተና ማድረግ ዋናው የሥራው የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚጠቁመው ይኸው ቡድን ከስያሜውና ለራሱ ከሰጠው የነቢይነት አክሊል ውጪ ሌላ ዝርዝር የማንነት መገለጫ ስለሌለው ጥሞናን ለሚያስቀድሙ ዜጎች ሁሉ “ማነህ ነቢዩ? እነማን ናችሁ ትንቢት አብሳሪዎቹ?” ወዘተ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አስገድዷቸዋል። ይህ ግራ አጋቢነቱ ቀድሞ መነጋገሪያ የሆነበት ማኅበር፣ ቡድን፣ የመናፍስት … [Read more...] about የኅቡዕ ቡድን ሪፖርት በኅቡዕ በሚሠሩ “ኢትዮጵያውያን” – ኢትዮጵያ ላይ የተመዘዘ ሰይፍ!
ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
"... አሁን ቱሪስት የለም" የላሊበላ ነዋሪ እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጋ ብርም ከዘርፉ ይገኝ ነበር የአማራ ክልል ቱሪዝም በግጭቱ ምክንያት ሥራ ለማቆም መቃረቡን የክልሉ የባህልና የቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ‼️ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዐማራ ክልልን ይጎበኛሉ ተብለው ከታቀዱት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር የመጡት 20 በመቶ ብቻ መኾናቸውን የገለጸው የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የክልሉ ቱሪዝም በእጅጉ በመዳከሙ ሥራ ለማቆም መቃረቡን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አየለ አናውጤ ትናንት ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት፣ “ዘርፉን ጨርሶ ለማስቆም እየተቃረበ ነው፤” ብለዋል፡፡ በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችም፣ በግጭቱ ሳቢያ ከሥራ ገበታ ውጭ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ (VOA) ጥር 7 2016 የታተመው … [Read more...] about ቱሪዝም በአማራ ክልል ሊቆም ነው
“መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? "አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ?በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው።የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም።በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል።መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመወጣትና የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት በምን ደረጃ ታቅዷል።" (አቶ አቤነዘር በቀለ - የተ/ም/ቤት አባል) " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ "ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም … [Read more...] about “መፈንቅለ መንግሥት በጭራሽ አይሳካም”
ትግራይ እየፈረሰች ነው – ሐይቲ በኢትዮጵያ
"አሁን ማንም ሰው ነው አግቶ የሚወስድህ፤ የሚጠብቅ የፀጥታ አካል የለም" ትህነግ በእብሪት ተሞልቶ መቀሌ መሽጎ በነበረበት ወቅት አገሪቱ በግጭት ስትታመስ፤ ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ ለውጡ ነውጥ ሆኖ ኢትዮጵያ በመፍረስ አደጋ ውስጥ ሆና ሳለ የሰላም ጉዳይ ያሳሰባቸው እናቶች ወደተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተጉዘው ነበር። በሁሉም ቦታዎች የክብር አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ የተጓዙት ወደ መቀሌ ነበር። የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ የሰላም ሠንደቅ በማውለብለብ እያለቀሱ መሬት ላይ ተደፍተው “ሰላም ላገራችን” ብለው ልመናቸውን ሲያቀርቡ የወንበዴው ቡድን መሪና በወቅቱ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እያላገጠ “እኛ ክልል ሰላም ነው፤ ይልቅ ሌላ ክልል ነው ሰላም የጠፋው፤ ስለዚህ እዚያ ብትሔዱ ይሻላል፤ እኛ ጋር ለምን እንደመጣችሁ አናውቀም?” በማለት ነበር … [Read more...] about ትግራይ እየፈረሰች ነው – ሐይቲ በኢትዮጵያ
ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ
ትሕነግ ሌላ ሕንፍሽፍሽ ይጠብቀዋል በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ጽንፈኛ የክልል ፓርቲ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ። ውሳኔው ትሕነግን ሕጋዊ ዕውቅና ሰጥቶ ወደ ብልጽግና ለመቀላቀል የታሰበ ነው የሚል ግምት ሲሰጠው በትሕነግ ውስጥ አንጃ ፈጥረው ፓርቲውን ቀውስ ውስጥ የከተቱት እነ ጌታቸው አሰፋና ሞንጆሪኖ በክልል የተወሰነ ጽንፈኛ ፓርቲ ይዘው ሊቀሩ ይችላሉ እየተባለ ነው። የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ። የሕጉ ዋና ዓላማ ትሕነግን ወደ ሕይወት ለማምጣት … [Read more...] about ትሕነግ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት ብልጽግናን ሊቀላቀል ይችላል ተባለ










