የሃይማኖትና የመንግሥትን መጣመር የሚደግፉም ሆነ ጥምረታቸውን በጽኑ የሚቃወሙ ጠንካራ የመከራከሪያ ነጥቦችን ያነሳሉ። ይህ ዘመናትን ያስቆጠረ ክርክር ባለንበትም ዘመን ሠለጠነ ከሚባለው ዓለም እስከ አገራችን የመወያያና የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። ይህ አጭር ጽሑፍ በሁለቱ ጽንፎች መካከል የሚካሄደውን ክርክር ለማቅረብ ወይም ለአንዱ ለመወገን ያሰበ ሳይሆን የሁለቱ ጥምረት ምን ውጤት አመጣ? ታሪክስ ምን ያስተምረናል? የሚለውን በጣም በጥቂቱ ለማንሳት ነው። ለማሳያነትም የክርስትና እምነትና መጽሐፍ ቅዱስ የምንጠቀም ሲሆን ይህ ማለት ግን ስለ ሌሎች ሃይማኖቶች ታሪክ ምንም አይልም በሚል እንዳይወሰድ አደራ ለማለት እንወዳለን። የሦስቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች አባት የሚባለው አብርሃም ይኖርበት ከነበረው ባቢሎን (የከለዳውያን ዑር) ወይም ያሁኗ ኢራቅ አካባቢ እግዚአብሔር … [Read more...] about የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?
Politics
“በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ
ሃራ ወይም ነጻ ተብሎ በሚጠራው መሬት ላይ ሠፍሮ የሚገኘው "የትግራይ የሰላም ኃይሎች" (TPF) ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሙሉ ትግራይን እንደሚቆጣጠር አስታወቀ። "ጸጥተኛ" ብለው ለሚጠሩት አቢዮት ሠራዊቱ እየተዘጋጀ እንደሆነም ተነግሯል። ይህ የተገለጸው በፈረንሳይኛ ቋንቋ በድረገጽ የሚታተመውና አፍሪክ XXI (Afrique XXI) የተባለው ጋዜጣ ከጥቂት ቀናት በፊት በትግራይ ላይ በሠራው ዘገባ ነው። ዘገባው በሃራ ምድር የሰፈሩትን የትግራይ የሰላም ኃይል/ቲፒኤፍ ተብለው ከሚጠሩት ታጣቂዎች ጋር ቃለ ምልልስ ካደረገ በኋላ ነው። የሰላም ኃይሉ አባላት በአብዛኛው ከዚህ በፊት በትህነግ ሥር ከነበረው የትግራይ መከላከያ ኃይል ወይም ቲዲኤፍ (TDF) ከሚባለው ከድተው የወጡ ናቸው። በተለይ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ በብዛት ከቲዲኤፍ እየኮበለሉ ወደ አፋር … [Read more...] about “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ
የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ
በቅርቡ “ሰማይ አንቀጥቅጥ” በሚል ስያሜ ተካሂዶ በቅብብሎሽ “የሻዕቢያ ተቀጣሪዎች” እና አፍቃሪ የትህነግ ሚዲያዎች ያራገቡት የበይነ መረብ ትዕይንት በዋናት የሻዕቢያና የበረከት ስምዖን ሤራ እንደሆነ ተሳታፊዎች አመልከቱ። ርዕዮት ዩቱብ ልዩ ገጸ ባህርይ ተዘጋጅቶለት ድራማውን ከልደቱ ጋር እንዲተውን የተደረገው ሆን ተብሎ እንደሆነም ተጠቁሟል። በአደባባይ ትህነግና ሻዕቢያን ለጆሮ በሚከብድ ቃላት የሚሳደበው የርዕዮት ዩቱብ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ ይህንን ገጸ ባህርይ እንዲጫወት የተደረገው ሆን ተብሎ ነው። የዜናው ባለቤቶች እንደሚሉት ቴዎድሮስ ከማንነቱ የተነሳ ለድራማው ተመራጭ አድርጎታል። ይህ ተፈጥሮው ታማኝ ስለሚያስመስለው ድራማውን በደንብ እየተጫወተ መሆኑም ተመልክቷል። የቴዎድሮስ ገጸ ባህሪ ልክ ልደቱ በ1997 ሕዝብ ጉድ እስኪል ኢህአዴግን እየተሳደበ በመጨረሻ ይፋ ከሆነው … [Read more...] about የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ
“ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
ልደቱ አያሌው ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር ያስተባበረው “አየር አንቀጥቅጥ” ትዕይንት ቅዳሜ ቀን ተካሂዷል። ልደቱ በስተመጨረሻ እንዳለው ከታሰበው በላይ የተሳካው የአየር ትዕይንት 15 ሰዎች ተናግረዋል፤ ሕዝብ በሳተላይት እና በተገኘው መንገድ ሁሉ ሰምቷል ብሏል። አገዛዙ ፈርቶ ኢንተርኔት አፍኗል፤ ዳታ ታቅቧል፤ ዩትዩብ እንዳይሠራ ተደርጓል ብለው ልደቱም፣ ቴዎድሮስም እየደጋገሙ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ይህ የአየር ላይ ትዕይንት “ስልቴዎች” ማለትም ስብሃት፣ ልደቱ፣ ቴዎድሮስ በልዩ ሁኔታ የቀመሩትና ትህነግን በመታደግ ለሻዕቢያ የተሠራ ልዩ የስልቴዎች ስልት ነው። ንግግር ያደረጉት ሰዎች ጥቂቶቹን ስንቃኝ፤ … የድግሱ መሪ ቴዎድሮስ መደረጉ በራሱ ብዙ የሚለው ነገር አለ። ቴዎድሮስ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ወገኖቼን (የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ወያኔዎችን) የፈጀች ኢትዮጵያ ጥንቅር … [Read more...] about “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ)
ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …?
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “አሉኝ” የሚላቸውን መረጃዎች የሚያሰራጭበት ሚዲያ በመኖርና በመጥፋት መካከል እንደሆነ ጠቅሶ የተለያዩ አማራጮችን ሲያቀርብ የነበረው ኤሊያስ መሠረት በተቃውሞ ሽፋን ለብልጽግና እየሠራ እንደሆነ መቅመጫቸውን ኬኒያ ያደረጉ ክፍሎች ገልጸዋል። በአገር ቤት ያሉና ይህንኑ ዜና የሚደግፉ ተጨማሪ ማስረጃዎችን በመገጣጠም ዜናውን አጉልተዋል። ኤሊያስ መሠረት በተቃውሞ ሽፋን ለብልጽግና እንደሚሠራ መረጃ የሰጡት ክፍሎች ኤሊያስ መሠረት ናይሮቢ በከተመበት ወቅት በቅርበት የሚያውቁት ናቸው። ትህነግ በሥልጣን በነበረበት ዘመን በሥልት ዜናዎችን ሲያቀዛቅዝና ሲያድበሰብስ ጠንቀቀው የሚያውቁት ወዳጆቹ እንደሚሉት፣ ኤሊያስ መሠረት ወደ ብልጽግና የመሸጋገር ዝንባሌ የታየበት “ትህነግ ዳግም ይመለሳል” የሚለው ምኞቱ ሙሉ በሙሉ መክሰሙን ከተረዳ በኋላ ነው። ለትህነግ … [Read more...] about ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …?
በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ
መለስ ዜናዊ ከስሙ ጀምሮ ሁሉ ነገሩ የውሸት ወይም ፌክ ነው። ላደረሰብን ግፍ እንክሰሰው እንኳን ብንል በየትኛው ስሙ ነው ፍርድ ቤት የምናቆመው የነበረው? ደግነቱ ከዚህ ሁሉ በፊት ወደ ዕረፍቱ ሄዶ እኛንም አሳረፈን። መለስ የዕውቀት ችግር አልነበረውም፤ ዕድሜ ለኢትዮጵያ ከሥር መሠረቱ በነጻ አስተምራዋለች። ንጉሡም ሰው ነው፤ ነገ ሀገር ይጠቅማል ብለው ሸልመውታል ይባላል። ግን ያልታከመና ሥር የሰደደ የበታችነት ስሜት የነበረው፣ አስተሳሰቡ ደሃ የሆነ ሰው ነበር። በዚህ ደሃ አስተሳሰቡ ነበር ኢትዮጵያን ለመምራት ሥልጣን ኮርቻ ላይ የተፈናጠጠው። ሥልጣን፣ ሃብት፣ ድሎት፣ ወዘተ ቢመጣም አስተሳሰብ ደሃ ከሆነ ችግሩ ውስብስብና መፍትሔ ዓልባ ነው የሚሆነው። መለስ ኢትዮጵያን በጣም ነበር የሚጠላት፤ ለማፍረስ ይፈልግ ነበር ለማለት ብዙም አያስደፍርም። ነገርግን ልክ እንደ … [Read more...] about በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ
ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው?
ከሰሞኑን ከትግራይ ክልል አንድ ምሥጢራዊ ሰነድ ሾልኮ ወጥቶ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። በማኅበራዊ ሚዲያዎችም በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ። ምሥጢራዊ ሰነዱ ፥ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር (በብዛት ኤርትራውያን በሕገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር የሚመለከት) እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የተጠና ሰነድ ሲሆን በ4 ክፍሎች የተከፋፈሉ 69 ገፆች አሉት። በሰነዱ በጥናት የተለዩ የወንጀል ተግባራት ፦* ሥልጣን ያለአግባብ በመጠቀም* በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በመያዝና በማዘዋወር (መኒ ላውንደሪንግ money laundering)* ሰው ማፈንና መሰወር* በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ከአገር ወደ አገር ማዘዋወር* የመንግሥት ስራ ምቹ ባልሆነ መንገድ መምራት* ኃላፊነት ባልተገባ መንገድ በመጠቀም* ሙስናመፈፀማቸውን ያረጋግጣል። በሰነዱ በተጠቀሱ የወንጀል ተግባራት በሠራዊት አመራር ያሉ … [Read more...] about ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው?
የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ
የእስክንድር አፋሕድ ጥሪ አቀረበ ለበርካታ ወራት ኅብረት ለመፍጠር ታስቦ ሲሠራበት የቆየው የአማራ ፋኖ ኅብረት በቋራ ጎንደር መመሥረቱ ተሰምቷል። የኅብረቱ ዓላማና ግብ ወደ አንድነትን ለማምጣትና የተቀናጀ ጥቃት ለመሰንዘር ሳይሆን ዓቅምን አስተባብሮ ለድርድር ለመቅረብ የታለመ እንደሆነ እየተነገረ ነው። እስክንድር ነጋ የሚመራው አፋሕድ ባወጣው መግለጫ “ከተቻለ እንዋሃድ፣ ካልሆነም አንቀናጅ ካልሆነ ቢያንስ እናበብ” ብሏል። ከጎንደር፣ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎጃም የተሰባሰቡ የፋኖ አመራሮች ባደረጉት ውይይት አንድ የፋኖ አደረጃጀት መመሥረታቸውን ተናግረዋል። ስሙንም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በማለት መሰየማቸውን አስታውቀዋል። የወጣው መግለጫ እንደሚለው “የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ - አማራ)፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የአማራ ፋኖ … [Read more...] about የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ
የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል”
“ሕገመንግሥቱ ያልፈለገ በሰላም ይሰናበታል” ብለው አለቆች ባስተማሩት መሠረት ትግራይ ከፌዴሬሽኑ መቀጠል አልፈልግም ስትል ይህንኑ ለምን ተግባራዊ አላደረገችም? ለምን ጦርነት ውስጥ ገባች? ምን ተፈልጎ ነው ወደ ጦርነት የተገባው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አለመኖሩ የኬሪያ ኢብራሒም ጥያቄ ነው። አንቀጽ 39 ተጠቅሶ መገላገል እንደሚቻል በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረ ድርጅት፣ ለዚሁ ህግ ጠበቃና ብቸና ሞግዚት ሆኖ የኖረ ፓርቲ ለምን ይህን ሁሉ ወጣት በነጻነት ሰበብ አስጨረሰ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ምላሽ መስጠት ለማይፈልጉና ለሚያድበሰብሱ ኬሪያ “አስቡና መልሱን ወዲህ በሉኝ” የሚል እንደምታ ያለው መረጃ ሰንዝረዋል። ጦርነቱን አስመልክቶ የትህነግ ጠበቃና ተከላካይ ሆኖ የዘለቀው ጠያቂያቸው ዝም ብሎ ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይጠይቅ ያለፈው ይህ አንኳር ነጥብ ውሎ አድሮ አጀንዳ እንደሚሆን … [Read more...] about የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል”
ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው
በትግራይ የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ያኮረፈው ሻዕቢያ ከግብጽ በወሰደው ውክልና “አንጃ” ከሚባለው የትህነግ ውስን ኃይልና በአማራ ኦሮሚያ ክልል ጠብ መንጃ ካነሱ ኃይሎች ጋር ግንባር ገጥሞ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊከፍት ያሰበውን ውጊያ በአቅም ማነስና ምድር ላይ ባሉ እውነታዎች አስገዳጅነት ለማራዘም መወሰኑ ተሰማ። የኤርትራን የጦርነት ዝግጅት ከውስጥና ከውጭ የሚከታተሉ የኢትዮሪቪው የመረጃ ሰዎች እንዳሉት፣ ከግብጽ በወሰደው ውክልናና ከግል ስጋቱ በመነሳት ከኤርትራ ውጭ በኢትዮጵያ ግዛት ሊጀመር ያሰበውን ጦርነት ለማቆየት የወሰነው ምድር ላይ ባሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ሳቢያ ዓቅሙ እንደማይፈቅድ ተረድቶ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት “ጦርነት አንፈልግም። ከነኩን ግን ምላሹ የከፋ ይሆናል” ማለቱ የሚታወስ ነው። እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ የመጀመሪያው ምክንያት በትግራይ … [Read more...] about ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው










