ቴዲ አፍሮን የሚወዱት ሰዎች እጅግ በርካታ የመሆናቸውን ያህል ጥቂት የማይባሉ ደግሞ አምርረው ይጠሉታል። ደጋፊዎቹ በተለይ በዘመነ ትህነግ በድፍረት የሚያዜማቸውን እያነሱ “የአንድ ሰው ሠራዊት” ይሉታል። የሚጠሉት ደግሞ ቴዲ “ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?” ቢል እንኳን “ይሄ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ፣ …” በማለት የስድብ ናዳ ያወርዱበታል። ቴዲ በትህነግ ዘመን ግልጽ ግፎች ደርሰውበታል። የሙዚቃ ኮንሰርቶቹ ያለ ምንም ካሣና ቅድመ ማስታወቂያ ቲኬት ከተሸጠ በኋላ በተደጋጋሚ ተሰርዘውበታል። የጎዳና ተዳዳሪ ገድለሃል በሚል ክስ ለእስር በተዳረገበት ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረበ ቁጥር ያለማቋረጥ እያለቀሰ ንጹሕ መሆኑን ለማሳመን ሞክሯል። ከእስር የተለቀቀበት አግባብም በራሱ ብዙ ሊያስብል የሚችል ነው። በአገራችን የለውጥ መዓበል በተነሳበት ወቅት ጃዋርን ጨምሮ አክራሪና ጽንፈኛ ኦሮሞዎች … [Read more...] about “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ
Archives for June 2022
“የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ)ን ማንነት የማያውቅ አንድም በሟቾች ይሸቅጣል፤ በደማቸው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይጣጣራል፤ ወይም ያወቀ መስሎት ይለፈልፋል፣ ይዘልፋል፣ ይዘፍናል። ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምህረት የማያውቅ እንደሆነ "ነጻ አወጣሃለው" ባለው ሕዝብ ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መመልከት በቂ ነበር። ስለምንረሳና እንደምረሳ ስለሚያውቅ ገድሎ ሙሾ አውራጅ ሆኖ ይመጣል። ጨፍጭፎን ስለ ሰላም ልደራደር ይላል። በወለጋ የተከሰተውንና መቼም የማይረሳውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በትህነግ ልክ ያለ አካል እና እርሱ አቡክቶ ጋግሮ የሠራው ኦነህ ሸኔ ካልሆነ ማንም ሊያደርገው እንደማይችል መገመት የማይችል ገና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልገባው የፖለቲካ ሕጻን ነውና አርፎ ተቀምጦ ይማር። ሌሎች ግን አሉ አዛኝ መስለው አጀንዳ የሚፈጽሙ። ባደባባይ ከሰቆቃው ሰለባ በላይ … [Read more...] about “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ
1. የገዳ ሥርዓት ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች (Primitive Oromo pastoral tribes) ለከብቶቻቸው ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና የውሃ ምንጭ (natural resources) ለማግኘት ጎረቤቶቻቸውን ይወሩበት የነበረ ባህላዊ አደረጃጀት ሲሆን ጉዲፈቻና ሞጋሳ ደግሞ የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋን በተወረረው ማኅበረሰብ ላይ ለመጫን የሚያገለግሉ ማስፈጸሚያ ስልቶች ናቸው። የአርብቶ አደሩን ማኅበራዊ፣ ወታደራዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ፣ የሚያደራጁ፣ ተዋጊዎችን ለጦርነት መርቀው የሚልኩና በመሳሰሉት የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ የስርዓቱ የገዢ መደቦች አባ ገዳ፣ አባ ዱላ፣ አባ ላፋ፣ ሞቲ፣ ሉባ ወዘተ ተብለው ይጠራሉ። የገዳ ሥርዓት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነው አርብቶ አደር ብቻ የሚያገለግል የአንድ ማኅበረሰብ ባህላዊ አደረጃጀት … [Read more...] about የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ
“የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል
የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየመከሩ ነው። የጎንደር ከተማን ሰላምና እድገት ለማረጋገጥ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች የጋራ አቋም ለመያዝ ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ያለው። ጎንደር የስልጣኔያችን ምልክት፤ የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሐብቶች መናገሻ የኾነች የዓለም መዳረሻ ከተማ መኾኗን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገጽታዋን ለማጠልሸት በሐይማኖትና በብሔር ሽፋን ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ሐይሎች መበራከታቸውን ገልጸዋል። በቅርቡ በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭትም የሕዝቡን ማኅበራዊ እሴት የማይመጥን … [Read more...] about “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል
የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ በኅልውና ዘመቻ እና በዘመቻ ለሕብረብሔራዊ አንድነት የግዳጅ ወቅት ከፍተኛ ጀግንነት ለፈጸሙ የመምሪያው አባላት የዕውቅናና የምስጋና መርኃግብር አካሂዷል። በመርኃግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ እንደተናገሩት አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ሀገርን ከውድቀት ለመታደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። መምሪያው በቀጣይ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በጀግንነት ለመወጣት ይበልጥ ዝግጁ መኾን እንደሚገባውም ምክትል አዛዡ አሳስበዋል። የዕዙ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ በበኩላቸው ክፍሉ በግዳጅ አፈጻጸም ወቅት … [Read more...] about የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው
ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርና የስነ ጽሁፍና ፎክሎር መምህሩ ብርሃኑ አሰፋ (ዶ/ር) ሀገራችን ኢትዮጵያ ረዥም ዘመናትን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ የመጡ በየአከባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ባህላዊ የግጭት አፈታትና የእርቅ ተቋማት አሏት ብለዋል። ለአብነት በወሎ አከባቢ ያሉትን ብናነሳ በራያና አከባቢው ዘወልድ፣ በተሁለደሬና አከባቢው አበጋር፣ በምዕራብ ወሎ አማሬና በሀብሩ አከባቢ ሸህ ለጋን መጥቀስ ይቻላል ያሉት መምህሩ በየአከባቢው ያሉት የግጭት አፈታቶቹ እንደየአከባቢው ባህል፣ ልማድ፣ እምነት እና የአኗኗር ኹኔታ መጠሪያቸውና የአከዋወን ኹኔታቸው ቢለያይም ግጭትን የመፍታትና እርቅን የማውረድ እሳቤያቸው ተመሳሳይ ነው ብለዋል። እነዚህ የግጭት መፍቻ ተቋማት በማኅበረሰቡ እምነትና ስነ ልቦና ላይ የተመሰረቱና አስታራቂዎቹም … [Read more...] about ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ። ፕሮጀክቱ “አሉሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ” የተሰኘ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ያዋለ ሲሆን÷ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ቴክኖሎጂውን በማላመድ ግንባታውን በፍጥነት ያከናወኑበት መሆኑም ተገልጿል። ቴክኖሎጂው የግንባታ ጥራትና ፍጥነትን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ ኮርፖሬሽኑ ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ አስር ወለል ያላቸውን 16 ህንጻዎች ያየዘ የመኖሪያ መንደር መገንባት ችሏል። የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ጥብቃ ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ መኪና ማቆም የሚያስችል ስፍራ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር፣ የልጆች መጫወቻና መዋኛ ገንዳን ያካተተ መሆኑም … [Read more...] about የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ ሃይል ጉዳት የደረሰበት የመልካ ጉባ ድልድይ መገንባት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በቦታው የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ተናገረዋል። የድልድዩ መሰራት ሰራዊቱ በዳዋ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመፈፀም የነበረበትን ተግዳሮት የፈታ የግንባታ ሂደት መሆኑም ተጠቅሷል። በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ብርጌድ አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ብርሃነ ልጃለም እንዳሉት ከዚህ ቀደም የሸኔን ታጣቂ ሃይል ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ የዳዋ ወንዝ ከፍተኛ ለተልዕኮ ችግር እንደነበር አውስተው የድልድዩ ግንባታ ፈጣን፣ ተወርዋሪና በሁሉም ቀጠናዎች ተንቀሳቅሶ ለድል የሚበቃ ሰራዊት የመገንባት አንድ አካል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል። በዕዙ የሬጅመንት አዛዥ የሆኑት ሻለቃ ገበረ ጋሞ በበኩላቸው ግንባታው የሰራዊታችን ድካም በመቀነስ … [Read more...] about በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት
ጃዋር የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙ ሕገወጥ ነው ሲል የዳውድ ኦነግ ከሰሰ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው አንዱ ኦነግ ጃዋር መሐመድ ገለቶማ በሚለው የአውሮጳና የአሜሪካ ስብሰባ ላይ የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙን ኮነነ። ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠቀም ትዕዛዝ አዘል ደብዳቤ ለኦፌኮ ጻፈ። በዳውድ ኢብሳ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተብሎ የተመዘገው ፓርቲ ባንዲራዬን ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀመ ነው ሲል መረራ ጉዲና ለሚመራው ኦፌኮ ቅሬታውን አሰምቷል። ከሁለት ቀናት በፊት በተጻፈውና በዳውድ ኢብሳ በተፈረመው ደብዳቤ ጉዳዩ በሚለው ርዕስ ሥር በሕጋዊ መልኩ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግን ባንዲራ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መልኩ መጠቀሙን ስለማስቆም የሚል ነው። ደብዳቤው ሲያጠናቅቅም ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ … [Read more...] about ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት
ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር
ዶ/ር አብይ አህመድ በተለያዩ መድረኮች ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን በማያሻማ መንገድ በጠራ አገላለፅ ባረጋገጠበት መንገድ (የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ፊርማ ነው)፤ ወልቃይት በአማራ ክልል መንግስት ስር እየተዳደረ ባለበት ሁኔታ፤ ወልቃይትን አብይ አህመድ ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጥ ስለሆነ አማራ ከመከዳትህ በፊት ተነስ የሚሉ የግጭት ነጋዴዎች ድምፅ ማሰማት ሳይሆን ለእነሱ ጆሮ የሚሰጠው ሰው ቁጥር በዚህ ደረጃ መጠኑ መጨመሩ የሚያስደንቅና የሚያሳስብም ነው። እርግጥ ነው ጉዳዩ የማንም ሳይሆን የራሱ የመንግስት የPR ችግር የፈጠረው ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ ለአማራ እንቆረቆራለን ወይም እንታገላለን ከሚሉት በላይ በወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡን የዓመታት ጥያቄና ትግል እውቅና ሰጥቶ ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን የጠራ አቋሙን በአደባባይ አረጋግጦ ለሕዝቡ ጥያቄ የራቀ ሳይሆን … [Read more...] about ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር