ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣን ሞባይል ስልክን ከሌባ ላይ የገዛችን ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ንብረቱን ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ ግለሰቧ ከወንጀለኞች በተለያየ ጊዜ የገዛቻቸው ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮችን፣ ላፕቶፖችንና ታብሌት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አለምነሽ ፕላዛ አካባቢ አንድ ግለሰብ ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ አይፎን ፕሮ ማክስ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ። የግለሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የተሰረቀው ስልክ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የሞባይል … [Read more...] about ፖሊስ: የተሰረቁ ስልኮቻችሁን መጥታችሁ ውሰዱ
addis ababa
ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
በጦር መሳሪያ በመታገዝ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 4 ግለሰቦች ከ20 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተስፋዬ ጌታቸው፣ ተገኝ ሞቲ፣ ባይሳ ተስፋዬ እና አዱኛ ኦልጅራ የተባሉት ተከሳሾች በቡድን ተደራጅተው በለሊት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ተከሳሾቹ በተደጋጋሚ ጊዜ በፈፀሙት በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል መዝገብ ተደራጅቶባቸውና አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ጌታቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ ተገኝ ሞቲ በ23 አመት ፅኑ እስራት እንዲሁም … [Read more...] about ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል
የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ካቢኔው በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡ በዚህም መሰረት፡- 1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ 2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ … [Read more...] about የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ። ፕሮጀክቱ “አሉሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ” የተሰኘ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ያዋለ ሲሆን÷ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ቴክኖሎጂውን በማላመድ ግንባታውን በፍጥነት ያከናወኑበት መሆኑም ተገልጿል። ቴክኖሎጂው የግንባታ ጥራትና ፍጥነትን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ ኮርፖሬሽኑ ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ አስር ወለል ያላቸውን 16 ህንጻዎች ያየዘ የመኖሪያ መንደር መገንባት ችሏል። የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ጥብቃ ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ መኪና ማቆም የሚያስችል ስፍራ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር፣ የልጆች መጫወቻና መዋኛ ገንዳን ያካተተ መሆኑም … [Read more...] about የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
“ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” የአዲስ አበባ 363 አመራሮች
"ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ" በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ 363 አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል። በሽኝት መርሐግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ "አሸባሪው የህውሃት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ እኛ እያለን መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን አያፈርሷትም" ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ለህዝቦቿ አንድነት ሁላችንም እንታገላለን፤ ሞትም ቢመጣ ለኢትዮጵያ መሞት ክብር ነው ብለዋል ከንቲባዋ። ለኢትዮጵያ እና ለነፃነታችን እኛ ሁላችንም ዘማቾች ነን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለ መስዋእትነት ድል እንደማይገኝ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መሸነፍ የለም፤ አሁንም አንሸነፍም ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች። ጁንታው አይደለም ደሴ የትም ቢመጣ መጨረሻው መቃብር ነው ያሉት ከንቲባዋ በገባበት ሁሉ ገብተን እዚያው … [Read more...] about “ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” የአዲስ አበባ 363 አመራሮች
ጩኸት ያፈናት ከተማ
የድምጽ ብክለት መጨመር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለምሬት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ከመጠን ያለፉት ረባሽ ድምጾች፡- ከንግድ ትርኢቶች፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከምጽዋት ጠያቂዎች፣ ከጎዳና ላይ ንግድ፣ ከምግብና መጠጥ ቤቶች፣ ጋራዥ፣ እንጨት ቤት እና ብረት ቤትን ከመሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከፊልምና ሙዚቃ መሸጫዎች፣ ከተሽከርካሪዎች እና ከመሳሰሉት ይመነጫሉ፡፡ ለመሆኑ የድምጽ ብክለት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ጉዳት ያስከትላል? እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ አንስተናል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የባለሙያዎች አስተያየት እና የተጎጂዎች ሐሳብ ተካቷል፡፡ "የድምፅ ብክለት መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳል፣ ያስተጓጉላል፣ እንቅልፍ ይነሳል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣል፣ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋል።” የሚሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ጩኸት ያፈናት ከተማ
በበጀት ዓመቱ 272 ማንሆል ክዳኖች ተሰርቀዋል – የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በበጀት ዓመቱ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 272 ማንሆል ክዳን እንደተሰረቀበት አስታውቋል። ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ የፍሳሽ መስመሮች በመዲናዋ ተዘርግተዋል ያለ ሲሆን የፍሳሽ መስመሮቹን የፍሰት መቆጣጠሪያነት እና ጽዳት ለመከታተል የሚያስችል ማንሆሎች በመገንባት እንዲከደኑ ቢያደርግም 272 ክዳኖች በህገወጥ ሰዎች ተሰርቀዋል ብሏል። ይህም በፍሳሽ መስመሩ ላይ ባዕድ ነገር እንዲገባ በማድረግ የማጣሪያ ጣቢያዎች ህልውና እየተፈታተነ እንደሚገኝና ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡ ክፍት በሆነ ማንሆል ውስጥ ገብቶ ጉዳት እየደረሰበት እንደሆነ ገልጿል። ድርጊቱ ህገ-ወጥ ድርጊቱ የከተማዋን የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ላይ አደጋ የደቀነ መሆኑን በመረዳት ከምንም በላይ ህብረተሰብ እና የጸጥታ አካላት … [Read more...] about በበጀት ዓመቱ 272 ማንሆል ክዳኖች ተሰርቀዋል – የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
በአዲስ አበባ በ9 ወራት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የመንገድ ጉዳት ደርሷል
በመዲናይቱ በ9 ወራት ብቻ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመንገድ ኃብት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 179 የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲሰላ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ የመንገድ ኃብት ላይ በተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት ለጉዳት ተዳርገዋል። ከደረሱት የግጭት አደጋዎች መካከል 45 የሚሆኑት በቀለበት መንገድ ላይ ሲሆን ቀሪዎቹ 134 የሚሆኑት ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ የደረሱ አደጋዎች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል። (tikvahethmagazine) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በአዲስ አበባ በ9 ወራት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የመንገድ ጉዳት ደርሷል