“ሀገሬን እጠብቃለሁ፤ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ 363 አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በሽኝት መርሐግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ “አሸባሪው የህውሃት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ እኛ እያለን መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን አያፈርሷትም” ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ለህዝቦቿ አንድነት ሁላችንም እንታገላለን፤ ሞትም ቢመጣ ለኢትዮጵያ መሞት ክብር ነው ብለዋል ከንቲባዋ።
ለኢትዮጵያ እና ለነፃነታችን እኛ ሁላችንም ዘማቾች ነን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለ መስዋእትነት ድል እንደማይገኝ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መሸነፍ የለም፤ አሁንም አንሸነፍም ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች።
ጁንታው አይደለም ደሴ የትም ቢመጣ መጨረሻው መቃብር ነው ያሉት ከንቲባዋ በገባበት ሁሉ ገብተን እዚያው እቀብረዋለን ብለዋል።
በዛሬው የመጀመሪያ ዙር 363 አመራሮች ሽኝት የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይ ዙሮች ለመዝመት በርካታ አመራሮች እየተመዘገቡ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply