የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በበጀት ዓመቱ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 272 ማንሆል ክዳን እንደተሰረቀበት አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ከ1500 ኪሎ ሜትር በላይ የፍሳሽ መስመሮች በመዲናዋ ተዘርግተዋል ያለ ሲሆን የፍሳሽ መስመሮቹን የፍሰት መቆጣጠሪያነት እና ጽዳት ለመከታተል የሚያስችል ማንሆሎች በመገንባት እንዲከደኑ ቢያደርግም 272 ክዳኖች በህገወጥ ሰዎች ተሰርቀዋል ብሏል።
ይህም በፍሳሽ መስመሩ ላይ ባዕድ ነገር እንዲገባ በማድረግ የማጣሪያ ጣቢያዎች ህልውና እየተፈታተነ እንደሚገኝና ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡ ክፍት በሆነ ማንሆል ውስጥ ገብቶ ጉዳት እየደረሰበት እንደሆነ ገልጿል።
ድርጊቱ ህገ-ወጥ ድርጊቱ የከተማዋን የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ላይ አደጋ የደቀነ መሆኑን በመረዳት ከምንም በላይ ህብረተሰብ እና የጸጥታ አካላት ድርጊቱን በመከላከል ከባለስልጣኑ ጎን እንድትቆሙ ጥሪውን አቅርቧል። tikvahethmagazine
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply