በጦር መሳሪያ በመታገዝ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 4 ግለሰቦች ከ20 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ተስፋዬ ጌታቸው፣ ተገኝ ሞቲ፣ ባይሳ ተስፋዬ እና አዱኛ ኦልጅራ የተባሉት ተከሳሾች በቡድን ተደራጅተው በለሊት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ተከሳሾቹ በተደጋጋሚ ጊዜ በፈፀሙት በጦር መሳሪያ የታገዘ የዘረፋ ወንጀል መዝገብ ተደራጅቶባቸውና አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸው ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ጌታቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ ተገኝ ሞቲ በ23 አመት ፅኑ እስራት እንዲሁም 3ኛ ተከሳሽ ባይሳ ተስፋዬ እና አዱኛ ኦልጅራ ደግሞ እያንዳንዳቸው በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply