• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው

June 12, 2022 06:21 pm by Editor Leave a Comment

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ በኅልውና ዘመቻ እና በዘመቻ ለሕብረብሔራዊ አንድነት የግዳጅ ወቅት ከፍተኛ ጀግንነት ለፈጸሙ የመምሪያው አባላት የዕውቅናና የምስጋና መርኃግብር አካሂዷል።

በመርኃግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ እንደተናገሩት አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ሀገርን ከውድቀት ለመታደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

መምሪያው በቀጣይ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በጀግንነት ለመወጣት ይበልጥ ዝግጁ መኾን እንደሚገባውም ምክትል አዛዡ አሳስበዋል።

የዕዙ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ በበኩላቸው ክፍሉ በግዳጅ አፈጻጸም ወቅት የሠራዊቱ የጀርባ አጥንት በመኾን በርካታ አኩሪ ተግባራትን ፈጽሟል ነው ያሉት። በዚህም አዳዲስ ሞያተኞችን ከነባር የመገናኛ ባለሞያዎች ጋር በማቀናጀት ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ በጦርነቶች ከፍተኛ ልምድ ያካበተ እንደመኾኑ መጠን በዕውቀት እና ቁሳቁስ የሰው ኀይሉን በመገንባት ግዳጅ የመፈጸም አቅሙን አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

ሽልማት ከተበረከተላቸው የመምሪያው አባላት መካከል ሻምበል ዝናቡ በቀለ በአሸባሪው ትህነግ ተበጣጥሶ የነበረውን የግንኙነት መስመር በራሱ ጥረት ቀጥታ አዲስ አበባ ካለው የጦር ክፍል ጋር ግንኙነት የመሰረተ ጓድ በመኾኑ የ1ኛ ደረጃ ሜዳይ ተሸላሚ ኾኗል።

ሌላኛዋ ተሸላሚ አስር አለቃ አገሬ ያለው የዳታ እና ግንኙነት ባለሙያ ናት። የተሰጣትን ኀላፊነት በአስተማማኝ ብቃት የተወጣች በመኾኗ የ3ኛ ደረጃ ሜዳይ ተሸላሚ ለመኾን ችላለች።

በዕውቅናና የምስጋና መርኃግብሩ ሌሎች ተሸላሚ አባላቶችም የተካተቱ ሲኾን በቀጣይም የኢትዮጵያን ኅልውና ከሚፈታተንና ከሚቃጣ ማንኛውም አደጋ ሀገራቸውን ለመታደግ ቁርጠኛ እንደኾኑ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

በሌላ በኩል የአማራ ልዩ ኀይል ተከዜ ክፍለ ጦር አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ ኢትዮጵያን ለማዳን በተደረገው ትግል የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አመራሮች እና አባላቱ የእውቅናና የማዕረግና እድገት ሽልማት ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።

በሥነ ሥርዓቱ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣የአማራ ልዩ ኀይል ረዳት ኮሚሽነርና የክፍለጦሩ አዛዥ፣የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የተከዜ ክፈለ ጦር አዛዥ ኮረኔል አብጀው ተፈራ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት የከፈተውን ጦርነት ለመመከትና የአማራን ሕዝብ ከጥፋት፣ ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ በተደረገው ተጋድሎ ተከዜ ክፍለ ጦር ከሌሎች አሃዶች፣ ክፍለ ጦሮችና ከመላው የጸጥታ ኀይል ጋር በመጣመር ትልቅ ታሪክ ሠርቷል ብለዋል።

ክፍለ ጦሩ በተሰለፈባቸው አውደ ውጊያዎች ኹሉ ትልልቅ ጀብዱዎችን እየፈጸመ የዘለቀ ነው ያሉት አዛዡ በክፍለ ጦሩ ውስጥ የላቀ ጀብዱ ለፈጸሙ አመራሮችና አባላት የማበረታቻ ኒሻን ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል። የተሰጣቸው ሽልማትም በቀጣይ ለሚኖረው ተልዕኮ በሞራል ዝግጁ እንዲኾኑ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት።

ለአባላቱ የእውቅናና የማዕረግ እድገት ሽልማቱን ያበረከቱት የአማራ ልዩ ኀይል ረዳት ኮሚሽነር አዳነ አስማረ ማዕረጉ በብዙ ውጣውረድና ከፍተኛ መሥዋእትነት የተገኘ ነው ብለዋል።

“መንግሥት እውቅናና ሽልማቱን የሰጠው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ መኾኑን ተገንዝባችሁ ሊመጣ የሚችለውን ወረራ ለመቀልበስ ዝግጁ እንድትኾኑ አደራ እየሰጣችሁ ነው” ብለዋል ለልዩ ኀይል አባላቱ።

ሽልማት ከተበረከተላቸው የክፍለ ጦሩ አባላት መካከል ኢኒስፔክተር ፍትህአለው ሙሉ በፈጸሙት ጀብዱ በዕለቱ የሻለቃነት ማዕረግ አግኝተዋል።

ሻለቃ ፍትህአለው ‟በብዙ ጓዶች መሥዋእትነት እዚህ መድረሴን ባልዘነጋም በሽልማቱ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።

በቡያ፣ጠለምት፣አድርቃይ፣ብርብራ፣ቦዛ፣ብና ሜዳና ሌሎች አውደውጊያዎች ላይ እንደተሳተፉ ያነሱት ተሸላሚው በቀጣይ ለሚኖረው ማንኛውም ግዳጅ ሽልማቱ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸውና ዝግጁ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

ሌላኛው ተሸላሚ ኢንስፔክተር ጀጀው ፈረደ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይልን ለመደምሰስ በተደረገው ተጋድሎ የአማራ ልዩ ኀይል ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ተጣምሮ በርካታ ጀብዱውችን ፈጽሟል ብለዋል።በዚህ ውስጥም ተከዜ ክፍለ ጦር ሚናው ከፍተኛ ነበር ነው ያሉት።

ሽልማቱ በብዙ ጀግኖች መሥዋእትነት የተገኘ መኾኑን እረዳለኹ የሚሉት ተሸላሚው ‟የተሰውትን ጀግኖች ቃል ጠብቀን በቀጣይ ለሚኖር ግዳጅ ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሮልናል” ነው ያሉት።

ክፍለ ጠሩ አሸባሪው የትግራይን ወራሪ ቡድንን ለመደምሰስ ባደረገው ተጋድሎ ከጸጥታ ኀይሉ ጎን ተሰልፎ በስንቅ፣በውጊያና በሞራል ድጋፍ ላደረገው የሰሜን ጎንደር ሕዝብ፣ለፋኖ አባላትና ለሌሎች ግለሰቦች የእውቅና ወረቀት ሽልማት አበርክቷል። (አሚኮ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: amhara special force, endf, endf western command, mulualem admasu, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule