የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ በኅልውና ዘመቻ እና በዘመቻ ለሕብረብሔራዊ አንድነት የግዳጅ ወቅት ከፍተኛ ጀግንነት ለፈጸሙ የመምሪያው አባላት የዕውቅናና የምስጋና መርኃግብር አካሂዷል። በመርኃግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ እንደተናገሩት አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ሀገርን ከውድቀት ለመታደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። መምሪያው በቀጣይ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በጀግንነት ለመወጣት ይበልጥ ዝግጁ መኾን እንደሚገባውም ምክትል አዛዡ አሳስበዋል። የዕዙ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ በበኩላቸው ክፍሉ በግዳጅ አፈጻጸም ወቅት … [Read more...] about የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው
amhara special force
“የመከላከያ ጥምር ኃይልና ህዝቡ አሸባሪውን ቡድን እንደ እግር እሳት እየፈጁት ነው”
የመከላከያ ጥምር ሀይልና ህዝቡ አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች እንደ እግር እሳት እየፈጀው እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የሽብር ቡድኑ ለከፈተው አገርን የማፍረስ ጦርነት ለመመከት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በከፍተኛ ቁጭትና ወኔ ወደ ግምባር እየዘመቱ ይገኛሉ ብለዋል። የመከላከያ ጥምር ሀይልና ህዝቡ አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች እንደ እግር እሳት እየፈጀው እንደሚገኝም ገልጸዋል። አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ቢገባም አይወጣም ያሉ የደሴ ወጣቶች "እንደገና" ብለው በመደራጀት አሸባሪውን እየቀጡትና አካባቢያቸውንም በንቃት እየጠበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። (ኢፕድ) ከዚሁ ጋር … [Read more...] about “የመከላከያ ጥምር ኃይልና ህዝቡ አሸባሪውን ቡድን እንደ እግር እሳት እየፈጁት ነው”
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ እንደገባና አቀባበል እንደተደረገለት ቡለን ወረዳ አሳውቋል። የቡለን ወረዳ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ፥ "ለዘላቂ ሰላም የሚንቀሳቀሰው የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በቡለን ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል" ሲል ፅፏል። ወረዳው በአቀባበሉ ላይ የቡለን ወረዳ ወጣቶች፣ ነዋሪው፣ ማህበረስቡና የሴክተር መስርያ ቤት ሰራተኞችና አመራሩን ጨምሮ ከከተማው 1 ኪ/ሜትር ወጣ ብሎ በመሄድ አቀባበል አድርገዋል ሲል ገልጿል። የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደቡለን ወረዳ መግባቱ በወረዳው ያለውን የፅጥታ ችግር ለመፍታት፣ ማህበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ አስተዋጽዖ ያደርጋል ተብሏል። ቡለን ወረዳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ የፀጥታ ስጋት ካለባቸው ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ ጊዜ … [Read more...] about የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ