በወልዲያ ከተማ ለሶስት ወራት ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ የፋኖ አባላት ተመርቀዋል በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሰ ፋኖ ተገኝተው “የመንግሥትን ጥሪ ተቀብሎ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሰለፍ በርካታ ውጤቶችን አምጥቷል” ሲሉ ተናግረዋል። ፋኖ ምሬ ወዳጆ በበኩሉ “የተጋረጡብነን ችግሮች ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአንድነት እንወጣዋለን” በማለት መልዕክት አስተላልፏል። (የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ
fanno
“የመከላከያ ጥምር ኃይልና ህዝቡ አሸባሪውን ቡድን እንደ እግር እሳት እየፈጁት ነው”
የመከላከያ ጥምር ሀይልና ህዝቡ አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች እንደ እግር እሳት እየፈጀው እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የሽብር ቡድኑ ለከፈተው አገርን የማፍረስ ጦርነት ለመመከት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በከፍተኛ ቁጭትና ወኔ ወደ ግምባር እየዘመቱ ይገኛሉ ብለዋል። የመከላከያ ጥምር ሀይልና ህዝቡ አሸባሪው ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች እንደ እግር እሳት እየፈጀው እንደሚገኝም ገልጸዋል። አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ቢገባም አይወጣም ያሉ የደሴ ወጣቶች "እንደገና" ብለው በመደራጀት አሸባሪውን እየቀጡትና አካባቢያቸውንም በንቃት እየጠበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። (ኢፕድ) ከዚሁ ጋር … [Read more...] about “የመከላከያ ጥምር ኃይልና ህዝቡ አሸባሪውን ቡድን እንደ እግር እሳት እየፈጁት ነው”