የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ በኅልውና ዘመቻ እና በዘመቻ ለሕብረብሔራዊ አንድነት የግዳጅ ወቅት ከፍተኛ ጀግንነት ለፈጸሙ የመምሪያው አባላት የዕውቅናና የምስጋና መርኃግብር አካሂዷል። በመርኃግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱ እንደተናገሩት አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ሀገርን ከውድቀት ለመታደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። መምሪያው በቀጣይ የሚሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በጀግንነት ለመወጣት ይበልጥ ዝግጁ መኾን እንደሚገባውም ምክትል አዛዡ አሳስበዋል። የዕዙ ኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ወርቅነህ ነዳሳ በበኩላቸው ክፍሉ በግዳጅ አፈጻጸም ወቅት … [Read more...] about የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው