ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው (ሰኞ) ዕለት የተፈፀመውን አሳዛኝ ድርጊት መነሻ በማድረግ በመተከል ዞን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት አመራር አካላት ጋር በዞኑ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል። ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝተዋል። በዞን የተለየዩ አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ኮማንድ ፖስት ተደራጅቶ የራሱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም፤ አሁንም የዜጎች ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ መጥፋት መቀጠሉ ሪፖርት ቀርቧል። በዚህ አካባቢም ሆነ በሌሎች ሠላምና ፀጥታን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሴረኞችን ገመድ መበጣጠስ፣ ጠንካራ የህግ የበላይነት ማስከበር ህብረተሰቡ ራሱን የመከላከል አቅም እንዲኖረው ማድረግ ወሳኝ ተግባር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ … [Read more...] about የመተከል ዞን ሕዝብ ሊደራጅና ሊታጠቅ ይገባዋል – አቶ ደመቀ መኮንን