• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የመተከል ዞን ሕዝብ ሊደራጅና ሊታጠቅ ይገባዋል – አቶ ደመቀ መኮንን

October 13, 2020 12:05 am by Editor 6 Comments

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በዛሬው (ሰኞ) ዕለት የተፈፀመውን አሳዛኝ ድርጊት መነሻ በማድረግ በመተከል ዞን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት አመራር አካላት ጋር በዞኑ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝተዋል።

በዞን የተለየዩ አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ኮማንድ ፖስት ተደራጅቶ የራሱን ዕቅድ አዘጋጅቶ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም፤ አሁንም የዜጎች ህይወት በአሳዛኝ ሁኔታ መጥፋት መቀጠሉ ሪፖርት ቀርቧል።

በዚህ አካባቢም ሆነ በሌሎች ሠላምና ፀጥታን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር የሴረኞችን ገመድ መበጣጠስ፣ ጠንካራ የህግ የበላይነት ማስከበር ህብረተሰቡ ራሱን የመከላከል አቅም እንዲኖረው ማድረግ ወሳኝ ተግባር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው፤ በመተከል ዞን በተደጋጋሚ በሚከሰተው የፀጥታ ችግር የዜጎች ህይወት መጥፋት አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ ክስተት መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱን በፅኑ ኮንነዋል።

በቀጣይ ወንጀለኞችን እና ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አካላትን በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ ራሱን አደራጅቶ አስፈላጊውን ትጥቅ ታጥቆ የተጠናከረ የመከላከል አቅም መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኮማንድ ፖስት አመራሩ የተያዘው ዕቅድ በሁሉም አካባቢ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲደረግና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ መተማመን ፈጥሮ መደበኛ ህይወት እንዲቀጥል አሳስበዋል።

አቶ ደመቀ ሕዝቡ እንዲታጠቅ የተናገሩበት ዜና ዋና መሠረት ያደረገው በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት የ12 ዜጎች ሕይወት ማለፉ ከተሰማ በኋላ ነበር።

በማንዱራ ወረዳ ድኋንዝ ባጉና ቀበሌ ትናንት ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ገልጸዋል።

አቶ ጋሹ ዱጋዝ

ከሟቾቹ በተጨማሪ አንድ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ደርሶበት የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

ሦስት ሰዎች የአንድን ግለሰብ መሣሪያ ነጥቀው በመሠወራቸው ምክንያት በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ሓላፊው አስታውቀዋል።

በቀበሌው ውስጥ ነዋሪ የሆነ እና መሣሪያ የተነጠቀበት ግለሰብ ቤተሰቦች በፈጸሙት ድርጊት አማካኝነት የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ገልጸው፣ አጥፊዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አቶ ጋሹ ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭት በጠፋው የሰው ሕይወት የተሰማቸውን ኀዘን በመግለጽ መሣሪያ ነጥቀው የተሠወሩ ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች እስካሁን ያልተያዙ ግለሰቦችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ የጸጥታ አካላት እየሠሩም እንደሆነ ተጠቁሟል።

የተከሰተው ድርጊት በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም እንኳን ከጀርባ ተልእኮ ያላቸው ኃይሎች መኖር አለመኖራቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገ እንደሆነም አቶ ጋሹ  አሳስበዋል።

በቀጠናው በተደጋጋሚ ግጭቶች ሲስተዋሉ እንደቆዩ ቢታወቅም፣ ትናንት የተከሰተው የሰዎች ሞት ግን ብሔርን መሠረት ያደረገ እንዳልሆነም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው በሁሉም የጸጥታ አስከባሪዎች አማካኝነት የማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ባለበት ተረጋግት የዕለት ተዕለት ሥራውን እንዲሠራም መልእክት ተላልፏል። (©ምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት እና ኢዜአ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: metekel, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Andnet says

    October 13, 2020 05:17 am at 5:17 am

    ይህ መልኩን እየቀያየረ እምነትና ማንነት የጅምላ ግድያ (የአማራን አካባቢው ማጽዳት )ሆን ተብሎ በባለስልጣናት በጸጥታ ኃይሉ የሚፈጸም ለመሆኑ እየታወቀ አንድም እርምጃ የለም ለዚሁም ከወሬ ባለፈ በጊዜያዊ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ይህን ያህል ዜጎች ሲጨፈጨፉ የት ነበረ የክልሉ የፀጥታ ኃላፊ የሰጡት ምላሽ ከእውነት የራቀ ወንጀሉን ለመደበቅ ሆን ብሎ የታቀደ በመሆኑ ም/ጠ ሚንስትሩ ጀምሮ የክልል ከተጠያቂነት አያመልጡም በአንድ ወር ውስጥ ሕፃናት አዛወንት ባልቴቶች በተደጋጋሚ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በዝምታ ሳይሆን በአዋጅ ባካባቢው የሚኖሩት ዜጎች የሚፈፀምባቸው ለመከላከል የራሳቸው አመራርና አደረጃጀት በተሟላ ተጥቅ የመያዝ በመሬታቸው ያለ ስጋት መኖር ሲችሉ ብቻ ነው ።
    የአማራ አመራሮች ከራሳቸው የፍርሃት ቆፈን ተላቀው በተላላኪነት ገዳዮችን ከመ ለም ወጥተው እንመራዋለን የሚሉትን ሕዝብ መብትና ማንነቱን ማስከበር ካልቻሉ አደጋው የከፋና የተገኘ ሕዝብ ማእበል ከተነሳ ሀገሪቱን ወደ ከፋ ግጭት ሳይከታት በጥልቅ በማሰብ ባላቸው አቅም ሕጋዊና መሰረታዊ የማያወላውል ውሳኔ ከግድያና ከማፈናቀል እስካላስቆሙ ያዙትን የተከታይነት ስልጣቸን ለተፈፀመው ጭፍጨፋ ተጠያቂዎች ናቸው

    Reply
    • Genet says

      October 15, 2020 02:49 am at 2:49 am

      ሁልጊዜ የአማራ ክልል አስተዳዳሪዎች ለዘብተኞች ናቸው ላለፉት 2 ዓመታት ይኼ ሁሉ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል ጠንከር ያለ አቋም አሣይተው አያውቁም በጣም ይገርመኛል

      Reply
  2. Tesfa says

    October 14, 2020 07:56 am at 7:56 am

    ፍትጊያው በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ ብቻ ነው። ይህም አማራን፤ ባህሉን ቋንቋውን ህዝቡን አፈር ድሜ ማስገባት፡፡ የእምነት ተቋምን ድምጥማጡን ማጥፋትና በቦታው ራስን ማዘመን/ማሰይጠን ነው። ከዚህ ውጭ የሚለፈፈው ነገር ሁሉ መልሶ ማልቀስ ነው። ትላንት ተፈናቀሉ ተብሎ እንደገና ከሞት አምልጠው የተቋቋሙትን ነው አሁን ወያኔና የኦሮሞ ባለጊዜዎች ከሌሎች ጋር አብረው የሚያርዷቸውና ተራፊዎቹን የሚያባርሩት፡፡ የሃበሻው ምድር ካበደ ቆይቷል፡፡ የዘር ፓለቲካ ለማንም እንደማይጠቅም እየታወቀ ወንዝ በማያሻገር ቋንቋና ለህዝብ በማይጠቅም ኋላ ቀር ባህል በመታጀብ ክልሌ፤ ሃገሬና ምድሬ እያለ በራፉ ላይ ሰንደቅ አቁሞ እኛን ብቻ እዩን የሚለው የብሄር ፓለቲካ ሞሽላቃና ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ትላንት ለ27 አመታት ሃገር ሲያምሱ፤ ሲሸጡና ሲለውጡ፤ ሲዘርፉና ሲያዘርፉ የነበሩ ከአንድ ብሄር የወጡ የወያኔ ወስላቶችና ተለጣፊ ድርጅቶች አሁን ሃገር ለማቆምና ለማፍረስ ጎራ ለይተው ሲፋለሙ ማየት የሃገራችን የፓለቲካ ጅልነት አጉልቶ ያሳያል፡፡ ኢትዮጵያ ሱሴ ናት ያለው መደመርና የሃገር አንድነት ምን እንደሆነ አይገባኝም ማለቱ በቀቢጠ ተስፋ የኦሮሚያን ሪፕብሊክ ለማቆም ከሚቋምጡት ጋር በመጎዳኘቱ ነው፡፡ በሃገር ውስጥ አብደው ጨርቅ ያወለቁ የፓለቲካ ሙታኖች “ጊዜአዊ መንግስት ይቋቋም” ሲሉን የ 60ዎቹን መፈከር አሁንም እንዳነገቡና ባሉበት እንደሚዳክሩ ያሳያል እንጂ ሃገሪቱ ፍትሃዊ ምርጫ እንጂ ጊዜአዊ መንግሥት አያሻትም፡፡ የኦነጉ የእድሜ ልክ ፓለቲከኛ አቶ ዳውድ በኦሮሚያ ላይ ብቻ ምርጫ እንዲደረግ ስመ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ የጠባብ ብሄርተኞች እይታ ከወያኔና ከሻቢያ እይታ ጋር አንድ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ለዚያ ይሆን ትራፊ ወታደሮቹን ይዞ ከኤርትራ ወደ ሃገር ሲመለስ ወያኔ ለኦነግ ሰራዊት ከፍተኛ አቀባበል በትግራይ ያደረገለት? ሴራው ይቀጥላል፡፡ መገዳደሉ ይቀጥላል፡፡ ራስን ለማዳን ግን ጠቃት የሚደርስበት ህዝብ ተደራጅቶ መታጠቅ የሚያስፈልገው ለመሆኑ የደመቀ መኮነን ጥሪ አያሻም፡፡ ሁሌ የድረሱልን ጥሪ፤ ሁሌ ተፈናቀሉ ዜና፡፡ ሁሌ ሴት ልጆቻችን ታፈኑ ወሬ መቼ ነው ማቆሚያው፡፡ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ለማበዳቸው በሃገር ውስጥ የሚያመነጩት ግፍና ግድያ ሳይሆን በአለም ላይ ተበትነው የሚይደርሱትን አተላና ኋላ ቀር ተግባር ሰው ልብ ሊለው ይገባል፡፡ ግድቡ ስራው እንዲቆም ለአለም ባንክ ለተለያዪ መንግሥታት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጀርመን፤ እንግሊዝና ሌሎችም የአለም ክፍሎች በየሰበቡ ራሱን አስጠልሎ አማራ ከኦሮሚያ ይውጣ የሚል ጭንጋፍ ትውልድ ነው፡፡ አንተን ካለህበት ስርቻ ሁሉ እየለቀመ እስከ ልጆችህ ወደ ናፈቃት ኦሮሚያ ቢመልስህ ምን ይሰማህ ይሆን? የሃበሻው ፓለቲካ አተላ ነው፡፡ ተሻለ ስትለውም ቅራሪ ብቻ ነው፡፡ ለሰው ልጆች መብት፤ ስለ ጥቁሮች መጨቆን መታገሉን ትቶ አውቆ እንዳበደ ሰው ከራስ ጋር መላተምን እንደ ስልጣኔ ቆጥሮታል፡፡ ይህ ደግሞ ሁሉም ከንቱ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ትላንት ተዘረፍኩ ያለው ዛሬ ዘራፊ ከሆነ፤ ትላንት የታሰረው መልሶ አሳሬ ከሆነ ፍትህ ለህዝባችን እንዴት ሊመጣ ይችላል? አሁን ማን ይሙት ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ቆሟል? የአማራው ባለስልጣናት ለአማራ ህዝብ ይገዳቸዋል? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ አበው፡፡ ግን የሃገራችን ፓለቲከኞች ራሳቸውን በዘርና በቋንቋቸው ዙሪያ ካላስጠለሉ ዝንብና ቁሩን አይችሉትም፡፡ ለዚህ ነው የህዝብን ስምና ቋንቋ ለበደላቸውና ለዝርፊያቸው ሽፋን ያደረጉትና አሁንም በማድረግ ላይ ያሉት፡፡ መተው ነገሬን ከተተው ይላሉ አበው ነገር ሁሉ ወልጋዳ ሲሆንባቸው፡፡ የስንቶች ደም በከንቱ ፈሰሰ? ስንቶች ምድራቸውን ትተው ያለልባቸው በባእድ ሃገር አፈር ለበሱ/ ስንቶች ውሃ ላይ ሰጥመው ቀሩ? ስንቶች የአውሬ ራት ሆኑ? ስንቶች በአረብ ጭፍን እይታ ከእንስሳ ተቆጥረው በር ተቆልፈባቸው ተሰቃዪ? በመሰቃየት ላይ ስንቶ አሁን ይገኛሉ? የጠቁር ህዝብ ጠላቱ ራሱ ነው፡፡ የሚያስበው ሁሉ እኔ ብቻ በመሆኑ በአለም ላይ እንደ ጉድፍ ተቆጥሮ ሲነገድበትና ሲቀለድበት ይኖራል፡፡ አማራ መሆን፤ ኦሮሞ መሆን፤ የሃረር ወይም የትግራይ ልጅ መሆን ብቻውን መልካምነት የለውም፡፡ አብሮ መኖር አብሮ ሰርቶ ማደግ ግን በአለም ዙሪያ ሁሉ ያስከብራል፡፡ ሌላው ሁሉ ግራጫ ሃሳብ ነው፡፡ ይብቃኝ!

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    October 21, 2020 12:06 pm at 12:06 pm

    ኣቶ ደመቀ መኮንን እንደ ም/ጠ/ሚ፥ ኣላሰቡም ልበል? የመተከል ህዝብ ሊደራጅና ሊታጠቅ ይገባዋል። ብለው ኣስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። ሊታጠቅ? ሊታጠቅ? ልብ በሉ። ሊታጠቅ ይገባዋል?

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    October 22, 2020 02:17 am at 2:17 am

    ህልም ነው፥ ህልም
    ጭልጥ የሚል፥ እልም
    ቅዠት፥ ጋራን መቧጠጥ፥ ጭልም
    ሲነቁ፥ መዳረቅ፥ ከርተምተም።

    Reply
  5. Mulugeta Andargie says

    October 22, 2020 04:30 am at 4:30 am

    እንዴት ነው የምትሉት?
    ጥራኝ ዱሩ፥ ጥራኝ መውዜሩ ነው?
    ለምን በፍቅር፥ በሰላም ኣብረን ኣንኖርም?
    ውሃ ዋና የማይችል ሰው ሆናችሁብን።
    ፍቅር ማለት፥ ኣንዱ ለሌላው መጨነቅ፥ ቅን ማሰብ፥ መረዳዳት፥ መተጋገዝ፥ እንጂ፤ ለበጣማ ቀሳውስትም ይችሉበታል፤ እንኳን ፖለቲከኞች። ቅን እናስብ!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule