የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየመከሩ ነው። የጎንደር ከተማን ሰላምና እድገት ለማረጋገጥ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች የጋራ አቋም ለመያዝ ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ያለው። ጎንደር የስልጣኔያችን ምልክት፤ የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሐብቶች መናገሻ የኾነች የዓለም መዳረሻ ከተማ መኾኗን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገጽታዋን ለማጠልሸት በሐይማኖትና በብሔር ሽፋን ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ሐይሎች መበራከታቸውን ገልጸዋል። በቅርቡ በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭትም የሕዝቡን ማኅበራዊ እሴት የማይመጥን … [Read more...] about “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል