• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል

June 12, 2022 07:09 pm by Editor Leave a Comment

የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው የአማራን ህዝብ አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየመከሩ ነው።

የጎንደር ከተማን ሰላምና እድገት ለማረጋገጥ መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች የጋራ አቋም ለመያዝ ያለመ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ያለው።

ጎንደር የስልጣኔያችን ምልክት፤ የሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሐብቶች መናገሻ የኾነች የዓለም መዳረሻ ከተማ መኾኗን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገጽታዋን ለማጠልሸት በሐይማኖትና በብሔር ሽፋን ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ ሐይሎች መበራከታቸውን ገልጸዋል።

በቅርቡ በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭትም የሕዝቡን ማኅበራዊ እሴት የማይመጥን አሳዛኝ ድርጊት ነው፤ ማንም ይሁን ማን ጥፋተኞች መወገዝ አለባቸው፤ አጥፊዎች ለህግ ቀርበው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በተደረገው ጥረት ሕዝቡ ያሳየው ትብብርም የሚመሰገን ነው ብለዋል።

በአካባቢው በአማራና በቅማንት ሕዝብ መካከል ግጭት ተከስቶ ሕዝቡ እንዲደሳቆል የሚያደርጉትንና ለዘመናት በአብሮነት የኖረውን የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ለመለያዬት በተለየዩ ጊዜያት ግጭት ቀስቅሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን በጋራ ልንታገላቸው ይገባል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።

የሰው ታላቅነት የሚመዘነው ከውድቀት መነሳት በመቻል በመኾኑ ከዚህ በፊት የተፈጠሩትን ግጭቶች ምክንያታቸውን በመለየት ለመፍትሔዎቻቸውና ለቀጣይ አብሮነታችን የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይኖርብናል ነው ያሉት።

“አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊ መሆናችንን በመገንዘብ ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱ አካላትን አጋልጠን ለህግ ማቅረብ አለብን፤ ከዚህ በኋላ የጎንደርን ሰላም ለማናጋት የሚሰሩትን አምርረን ልንታገላቸው ይገባል ” በማለት ነው ያሳሰቡት ዶክተር ይልቃል።

በቅርቡ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ የተጀመረው የህግ ማስከበር ስራ የነበሩ ስጋቶችን በመቀነስ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።

የህግ ማስከበር ዘመቻው የአማራ ሕዝብን አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው ብለዋል።

አንድ ስንኾንና ስንጠናከር ሌሎች ያደምጡናል፤ ከተፈረካከስን ግን ተደማጭነታችን ይቀንሳል ሲሉም ለነዋሪዎች የአንድነት ጥሪ አቅርበዋል። (አሚኮ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: amhara region, operation dismantle tplf, wolkayit, yiliqal kefale

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule