ሕግ በረጅም ገመድ ያሰረው ጃዋር! ቅድሚያ “ኢትዮጵያዊ ፣ አባ ሜንጫ፣ አክቲቪስት፣ ተንታኝ፣ ፖለቲከኛ፣ አሁን ደግሞ “ሐጂ” ሆንኩ ያለው ጃዋር ማነው ነው? የሚለው ድብልቅልቅ ጉዳይ መመልከት ያሻል። ወይም የተለያዩ ማንነት ያለበት ጥያቄ መመለስ ግድ ነው። ጃዋር ወደ ፖለቲካ ሲመጣ በዳያስፖራ ያሉትን አገር ወዳዶች ለማማለል ፍጹም ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ በንግግሩ ሁሉን አስደምሞ ነበር ብቅ ያለው። ነገሮች መስመር ሲይዙለትና ደጋፊ ሲያገኝ እነዚህኑ ወደ ላይ የሰቀሉትን መሳደብና ኢትዮጵያን ማበሻቀጥ ጀመረ። በወቅቱ ተው ብለው አዛውንቱ የዳያስፖራ ምሁራን መከሩት። ወደላይ እየወጣ ስለነበር ይልቅ እኔን ብትሰሙ ይሻላል አላቸውና አልፏቸው ተስፈነጠረ። በቀጣይ ለኦሮሞን ትግል “አዲስ ትንፋሽ ነኝ” በማለት ራሱን መሪ አድርጎ ሾመ። የቀድሞ የኦሮሞ ታጋዮችን በተለይም ዕንቅፋት ይሆኑብኛል … [Read more...] about እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ?
Archives for June 2022
ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ
* ገና ከጅምሩ የመፈረካከስ አዝማሚያ እየታየባቸው ነው በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻ አውጪነትና በብሕር ድርጅትነት የሚታወቁ ሙሉ በሙሉ የተካተቱበት አዲስ የፓርቲዎች የምክክር ቤት (caucus) መቋቋሙ ተገለጸ። በስም ከተዘረዘሩት የምክክር ቤት አባል ድርጅቶች ውስጥ ከአፋር ሁለት፣ ከኦሮሚያ ሁለት፣ ከትግራይ አረና፣ የወላይታና የዶንጋ ሕዝቦች ይገኙበታል። በርካታዎቹ በምርጫ ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው ሲሆኑ በፓርቲ ደረጃ መድረክ ሲገኝ፣ በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ አንድ ድምጽ ያገኘው ሕብርም አለበት። ስብስቡ ገና ከጅምሩ የመፈረካከስ ሁኔታ እየታየበት እንደሆነ ተገለጸ። መንግሥት ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ጋር ሙሉ ውጊያ ገብቶ በነበረበት ወቅት ጡንቻ ያበቀሉ ያላቸውን እያጸዳና የሕግ ማስከበር እያካሄደ ነው በሚባልበት ወቅት ላይ፣ በተለይም በኦሮሚያና … [Read more...] about ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ
“አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ”
መከላከያ ሰራዊታችን በውጊያ ወቅት ሀገርና ህዝብ የሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነትና በድል ለመወጣት ሀሩር እና ብርዱ ሳይበግረው በየተራራው በየጥሻው ድንጋይ ተንተርሶ ሙቀቱን በላቡ ዝናቡን በሰውነቱ ሙቀት እየተቋቋመ ግዳጁን በድል ይወጣል። አንፃራዊ ሰላም ባለበት ደግሞ በደረሰበት ቦታ ሁሉ ህዝባዊ ሰራዊትነቱን በተግባር ያሳያል። ካለው የዕለት ጉርሱ ቀንሶ ለተቸገሩ ወገኖች ያካፍላል። በጉልበቱም በገንዘቡም ይረዳል። በምዕራብ ዕዝ በሚገኝ ክ/ጦር ሁለተኛ አባይ ሬጅመንት የሆነው እንዲህ ነው። ህፃን አማኑኤል ሽፈራው ይባላል። የ11አመት ታዳጊ ሲሆን ተወልዶ ያደገው በሰሜን ጎንደር አድዓርቃይ ወረዳ አምበራ አካባቢ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በሚባል ሰፈር ነው ። ህፃን አማኑኤል እንደሚለው እናቴ ትግራይ ለስራ እንደሄደች አልተመለሰችም። አባቴን አላውቀውም። ከአጎቴ ጋር ነበር … [Read more...] about “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ”