በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ 53 ሕገወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች ባለፈው እሁድ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ቀሬ ከተማ ኬላ ላይ መያዛቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበባየሁ ገረመው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦችና ሹፌር ያመለጡ በመሆናቸው እነሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አበባየሁ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ በልደታ ክ/ከተማ ተሠርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀልን ለመከላከል የክትትልና … [Read more...] about ሕገወጥ መሣሪያዎችና ተሠርቀው የተከማቹ የመኪና ዕቃዎች ተያዙ
Archives for September 2020
“ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
በተደጋጋሚ የክስ ቻርጅ እንዳይሰጠው ጥረት ሲያደርግ የነበረው ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከግብርአበሮቹ ጋር “ተከሳሽ” የሚለውን መጠሪያ ትላንት ሰኞ መስከረም 11/2013 ተቀብለዋል፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በይፋ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ በጃዋር መሐመድ እና ሌሎች 23 ተከሳሾች ላይ ክሱን በመሠረተበት ወቅት፤ ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ወንጀል ችሎት፤ በውሎው የክስ ሰነዶቹ ለተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲከፋፈል አድርጓል። በመሆኑም እነ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል። ዐቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ ላይ 10 ክሶችን … [Read more...] about “ተጠርጣሪዎቹ” እነ ጃዋር “ተከሳሽ” የተባሉበት ክስ ዝርዝር
የመከላከያ ሠራዊት በቤንሻንጉል አካባቢ ታጣቂዎች ላይ የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ ጀመረ
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግድያ በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ አሳስቧል የመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ በአካባቢው ግድያና ጥቃት በፈጸሙ ማንነታቸው በግልጽ ያልተነገረ ታጣቂዎችን የመደምሰስ ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ ጥቃት በተሰነዘረባቸው አካባቢዎች ላይም 150 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ስምሪት ማድረጉንም ገልጿል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዚህ ቀደም ለተደጋጋሚ ጊዜ እንዲሁም ሰሞኑን በነዋሪዎች ላይ በተቃጣው ግድያና ጥቃት ሥጋት ውስጥ የወደቁ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግሥት ደኅንነታቸውን በዘላቂነት እንዲያስጠብቅላቸው ጠየቁ። ነዋሪዎቹ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የሰሞኑን ግድያና ጥቃት ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን የተመራ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቡድን ባለፈው ዓርብ መስከረም 8 ቀን … [Read more...] about የመከላከያ ሠራዊት በቤንሻንጉል አካባቢ ታጣቂዎች ላይ የመደምሰስ እርምጃ መውሰድ ጀመረ
“ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመዲናዋ ካይሮና በአጎራባች ከተሞች ዛሬ (ሰኞ) ተካሄደ። በካይሮ ዳርቻ በምትገኘው የጊዛ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተቃውሞ ትዕይንት ያካሄዱት የፀጥታ ኃይሎችን ማስጠንቀቂያ በመጣስ ነው። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ካሰሙት መፈክር መካከል “ሲሲ ውጣ” እና “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” ("Sisi out" and "The people want to overthrow the regime")የሚሉት የማኅበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመንግሥት ተቃውሞ በላይ አንድ የፖሊስ መኪናን ያቃጠሉ ሲሆን በፖሊስ ላይ ድንጋይ የወረወሩበት ድርጊትን የሚያሳይ ቪዲዮም በማህበራዊ ሚዲያ ተለቋል። አልጀዚራ በዘገባው እንዳመለከተው የአሁኑ ተቃውሞ ከመቀስቀሱ በፊትም የፀጥታ ኃይሎች … [Read more...] about “ሕዝብ አገዛዙን መገልበጥ ይፈልጋል” የአልሲሲ ተቃዋሚዎች
“የሤራ ፅንሰ ሃሳብ በኢትዮጵያ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሁን ገዝፎ ወጥቷል” ዶ/ር ደመቀ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጭ ግንኙነት ትብብር እና ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ዶክተር ደመቀ አጭሶ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ በኢትዮጵያ የፈለገ ጥሩ ሃሳብ፣ ጥሩ አመለካከት ይዘህ ብትመጣ አንተን ለመቃረን ብቻ ሌላ ኃይል ተደራጅቶ ይጠብቅሃል። ይህ ማደም፤ ሴራ ነው። ይህ የሴራ ፅንሰ ሃሳብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ገዝፎ ወጥቷል። “የፈለገ ጥሩ ሃሳብ፣ ጥሩ አመለካከት ይዘህ ብትመጣ አንተን ለመቃረን ብቻ ሌላ ኃይል ተደራጅቶ ይጠብቅሃል”። ይህ የሴራ ፅንሰ ሃሳብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ገዝፎ መውጣቱን ዶክተር ደመቀ … [Read more...] about “የሤራ ፅንሰ ሃሳብ በኢትዮጵያ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አሁን ገዝፎ ወጥቷል” ዶ/ር ደመቀ
ኢትዮጵያ ሁለት የመዝናኛ ከተማዎችን ልትገነባ ነው
ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን ግቧ አካል የሆኑ ሁለት የመዝናኛ (ሪዞርት) ከተማዎችን ልትገነባ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የቱሪዝም እቅድ ዘርፍ መሪ አቶ አህመድ መሐመድ እንደተናገሩት፤ ከመዝናኛ ከተሞቹ አንዱ የሚገነባው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ነው። ግድቡ ሲጠናቀቅ 70 ገደማ ሰው ሰራሽ ደሴቶች ይኖራሉ። ግድቡ ሲጠናቀቅም በሀገሪቱ ዋነኛው የቱሪስት መዳረሻ ይሆናል። ሁለተኛው የመዝናኛ ከተማ የሚገነባበት ቦታ የአዋጪነት ጥናት ከተካሄደ በኋላ ይወሰናል ያሉት አቶ አህመድ፤ የመዝናኛ ከተማ ግንባታ የሚከናወነው የግሉ ሴክተርን ጨምሮ በብዙ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መሆኑንም ተናግረዋል። ሪዞርቶችን በግል ባለሀብቶች እንደሚገነባ የተናገሩት አቶ አህመድ፤ የመዝናኛ ከተማዎቹ ሀገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፍ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሁለት የመዝናኛ ከተማዎችን ልትገነባ ነው
ግምታቸው 14 ሚሊዮን ብር የሚጠጉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ከ13 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ሳይፈፀምበት ከመስከረም 4 እስከ 9/2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ማሽላና ስንዴ፣ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ ሲጋራ፣ በሕዝብ ማመላሻ ሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ የሽጉጥ ጥይት፣ በጭነት ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ የነበረ የክላሽ ጥይትና የሞባይል ስልኮች ይገኙበታል። በተጨማሪም ከሀገር ሊወጣ ሲሉ የተያዙ የቁም ከብቶች፣ የብር ጌጣጌጥ፣ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ ልባሽና አዳዲስ አልባሳት ይገኙበታል። የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ … [Read more...] about ግምታቸው 14 ሚሊዮን ብር የሚጠጉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ተከፈተ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን ዛሬ (እሁድ) መርቀው ከፍተዋል። ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች ሰው ሰራሽ የሆነ የማሰብ ክህሎትን በተለያዩ የስራ መስኮች የሚያሰማራ ቴክኖሎጂ ነው። ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ችለው ለሰው ልጅ አድካሚ የሆኑ ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን ያስችላል በማት ኢዜአ ዘግቧል። በኢትዮጵያም የተቋቋመው ማዕከል ለግብርና፣ የትምህርት፣ ጤና እንዲሁም ለህብረተሰብ ጥበቃና ደህንነት አገልግሎቶች ይውላል። ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም አሁን ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የጡት ካንሰርና የጭንቅላት ዕጢ መለየት በሚያስችሉ መተግበሪያዎች እየሰራ ይገኛል። ጎልጉል የድገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ተከፈተ
ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አቃቤ ሕግ በእነ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ቀን አርብ መስከረም 8፤ 2013ዓም ነበር። ሆኖም በዚህ ክስ ይመሰረታል ተብሎ በሚጠበቅበት የመጨረሻው ቀን ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። በዚህም አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ተናግረው ነበር። ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ መሠረት ጃዋርና ሲራጅ መሐመድና ግብረአበሮቹ በ10 ተደራራቢ ክሶች ፋይል እንደከፈተባቸውና የክስ ቻርጁም መስከረም 11፤2013ዓም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ እንደሚደርሳቸው አስታውቋል። ዐቃቤ ሕግ ያወጣው ጽሁፍ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድ፤አቶ በቀለ ገርባ፤አቶ ሀምዛ አድናን እንዲሁም በሌሉበት የተከሰሱትን የኦሮሚያ ሜዲያ … [Read more...] about ጃዋርና ግብረአበሮቹ 10 ተደራራቢ ክሶች ተከፈተባቸው
አራት መቶ ሺህ ዶላር የሚያወጣ ኮኬይን ቦሌ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ 400 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 4 ኪሎግራም ኮኬይን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በማይሰራ ላፕቶፕ ቦርሳ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቀጥጥር ሥር ውሏል። ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ በላፕቶፕ ቦርሳ ለማሳለፍ የሞከረው አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በኤክስሬይ ፍተሻ አማካኝነት የተያዘ ሲሆን፤ በወንጀል ድርጊቱ ተባባሪ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሌሎች ሶሰት ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል። በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉት አራት ተጠርጣሪዎችና አደንዛዥ ዕፁ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ … [Read more...] about አራት መቶ ሺህ ዶላር የሚያወጣ ኮኬይን ቦሌ በቁጥጥር ሥር ዋለ