ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ የመሆን ግቧ አካል የሆኑ ሁለት የመዝናኛ (ሪዞርት) ከተማዎችን ልትገነባ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የቱሪዝም እቅድ ዘርፍ መሪ አቶ አህመድ መሐመድ እንደተናገሩት፤ ከመዝናኛ ከተሞቹ አንዱ የሚገነባው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ነው። ግድቡ ሲጠናቀቅ 70 ገደማ ሰው ሰራሽ ደሴቶች ይኖራሉ። ግድቡ ሲጠናቀቅም በሀገሪቱ ዋነኛው የቱሪስት መዳረሻ ይሆናል።
ሁለተኛው የመዝናኛ ከተማ የሚገነባበት ቦታ የአዋጪነት ጥናት ከተካሄደ በኋላ ይወሰናል ያሉት አቶ አህመድ፤ የመዝናኛ ከተማ ግንባታ የሚከናወነው የግሉ ሴክተርን ጨምሮ በብዙ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሪዞርቶችን በግል ባለሀብቶች እንደሚገነባ የተናገሩት አቶ አህመድ፤ የመዝናኛ ከተማዎቹ ሀገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፍ የምታገኘው ገቢ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
እንደ አቶ አህመድ መሐመድ ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ በ2022 ኢትዮጵያን የቱሪስቶችን ቁጥር 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለማድረስ እቅድ የያዘች ሲሆን ፣ ከቱሪዝም ዘርፍ ብቻ የሚገኘውን ገቢ 23 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ አቅዳለች።
በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ በነባር 40 መዳረሻዎች ላይ እሴት በመጨመር በመላ አገሪቱ 59 አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለማልማት እቅድ መያዟን የተናገሩት አቶ አህመድ፤ ሚኒስቴሩ በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ የፈጠራ ማዕከላት እና የስብሰባ ማዕከላት ግንባታ እንደሚከናወን አብራርተዋል።
እንዲሁም እንደ ፣ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ ባህላዊ ምግብ እና መጠጥ ቤቶች ያሉ የቱሪስት ለቱሪስት አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት ግንባታ በቀጣይ 10 ዓመታት ለማካሄድ በእቅዱ ላይ መያዙን አቶ አህመድ አመልክተዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው፤ ከላይ ከተጠቀሱት ተግባራት በተጨማሪ ቅርሶችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ብሎም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም በመላ አገሪቱ የሚገኙ በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሶችን የማደስ ተግባር በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀዋል ።
የሰው ኃይልን ፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን፣ የመስመር ላይ አገልግሎት አሰጣጥን ፣ ዲጂታል ማድረግን እና የቱሪስት ገበያዎች ብዝሃነትን በማሻሻል በዘርፉ የመዋቅር ሽግግርን ለማምጣት ተጨማሪ ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ማብራሪያ፤ ሀገሪቱ በዘርፉ በቀጣይ 10 ዓመታት ለማሳካት ያቀደችውን እቅድ ለማሳካት በአገሪቱ ውስጥም ጥሩ ዕድሎች አሉ። እስካሁን በቱሪስት መዳረሻነት ያልታወቁ የመስህብ ስፍራዎች እና ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ናቸው በማለት መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ራሔል በቀለ says
ለኦሮሞ ሰፋሪ አመቻችተህ ስራ በመተከል ክልል ያለ ግድብ አማራ ብቻ ሚገደለው ሚስጥሩ ገብቶናል አዎ መጀመሪያ በዚህ 2 አመታት ለመኖር ያብቃን ከዚያ ብናወራ አይሻልም?