“ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው” በሚል ርዕስ አንድ ዘገባ ካወጣን በኋላ ዛጎል “በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። አሁንም የኢትዮጵያን መንግሥት ለማሳሰብ የምንፈልገው ይህንን የተቀናጀ ሥራ እያከናወኑ ያሉት ህወሓቶች መሆናቸውን ነው። ከዚህ ሌላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ድንበር ኬላዎች ከጎረቤት አገር ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይገባል ከሚለው እሳቤ በተጨማሪ በቦሌ በኩልም እየገባ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባዋል። ስለዚህ በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ በተጓዦች በተለይም በበረራ ሠራተኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል እንላለን። በአሜሪካ “ገንዘብ – ውሰዱልን” የቅርብ ወዳጆችን ግንኙነት በጠሰ “እንዴት ብትንቁን ነው” ሲል ባለቤት ቁጣ የተሞላ ምላሽ … [Read more...] about በቦሌ በኩል አሮጌው ብር እየገባ ነው፤ በበረራ ሠራተኞችና መንገደኞች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ
Archives for September 2020
“በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ እንዲሁም የፀና ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች አንዱ ጃዋር መሐመድ፣ እሱን ጨምሮ እስክንድር ነጋና ልደቱ አያሌው የተከሰሱት መንግሥት በምርጫ ያሸንፋሉ የሚል ሥጋት ስላለው እንጂ ወንጀል ፈጽመው አለመሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረ። ጃዋር ይኼንን የተናገረው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 260215 መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የከፈተውን ክስ፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተከሳሾች ሲሰጣቸው ነው። በሽብርተኝነት ሲከሰስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ የመጀመርያው በኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ የቀረበበት ክስ ሲሆን፣ ሁለተኛው አሁን የተከሰሰበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው … [Read more...] about “በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
ከ3.7 ሚሊዮን ብር በላይ በሰበታ ተያዘ
በሰበታ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ የተከማቸ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ተያዙ። የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የተያዘው ገንዘብ 3 ሚሊየን 751 ሺህ 830 የኢትዮጵያ ብር፣ 2 ሺህ 950 የአሜሪካ ዶላር እና የዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ የፓኪስታንና የኦማን ገንዘቦች ናቸው። በከተማው የ3ኛ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታደሰ ሁሪሳ ገንዘቡ በግለሰብ ቤት ውስጥ አልጋ ስር ተከማችቶ የተያዘው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅር ክትትል ነው ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ወደ ፊትም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ቀነኒሳ ዳዲ … [Read more...] about ከ3.7 ሚሊዮን ብር በላይ በሰበታ ተያዘ
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች በወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ፤ ለተጠርጣሪዎች ተፈቅዶ በነበረው ዋስትና ላይ ፖሊስ የመልስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለመጪው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 19 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የተጠርጣሪዎችን አቆያየት በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በጠዋት ችሎት ቀርበው የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች አልተገኙም በሚል ብይኑን ለዛሬ ማሳደሩን ጠበቃው ገልጸዋል። እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሲጠብቁ የቆዩ ሰባት ተጠርጣሪዎችም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሐዋሳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው ክስ የሕዝብ ሰላምንና የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል፣ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝና የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል በማለት የዋስትና መብታቸው እንዳይፈቀድላቸው መከራከሩን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡት እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ መንግሥት ወይም ዓቃቤ ሕግ ለሕዝብ ሰላምና ለአገር ደኅንነት የሚያስብ ከሆነ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው፣ በመጪው አገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ መደረግ እንዳለበት ለፍርድ ቤት ተናገሩ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ዋስትና እንዲከበርላቸው የጠየቁት፣ የተመሠረተባቸውን ክስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ተግባራትና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ካነበበላቸው በኋላ፣ ስለመብት … [Read more...] about የእነ እስክንድር ክስ እንዲሻሻል ተጠየቀ
ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው
በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የገንዘብ ኖት ለውጥ ተከትሎ መደናገጥ ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን እያስገባ እንደሆነ ተጠቆመ። ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፤ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ። ጭንቅላቱ የደረቀውና ኪሱ ወደ በመድረቅ ጉዞ ላይ ያለው ህወሓት የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገባ ጎልጉል ያጠናቀረውን መረጃ ለንባብ አብቅቶ ነበር። ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከምኒልክ ቤተመንግሥት የተባረረው ህወሓት መቀሌ በየሆቴሉ መሽጎ በኢትዮጵያ የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህንንም ተግባሩን ለማስፈጸም እንዲረዳው በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ ሐሰተኛ የብር ኖቶች በማተም ተግባር፤ በኮንትሮባንድ ንግድ፤ ገንዘብ ከአገር በማሸሽ፤ ወዘተ ሕገወጥ ተግባራት … [Read more...] about ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው
ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
በኢትዮጵያና በውጪ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ በማሰራጨትና የበርካታ ሰዎችን ትኩረት በመሳብ በርካታ ገቢ የሚያስገኝ ተከታታይ መሰብሰብ ያልተለመደ ተግባር አይደለም። በተለይ ግን ብዙ ተከታይ አለን በሚሉ ዘንድ ይህ በተደጋጋሚ ሲከሰት መስተዋሉ የሞራልም የስብዕናንም መዝቀጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው። ህወሓት በአገራችን ሕዝብ ላይ ካደረሰው የግብረገብነት ዝቅጠት ወደ ተሻለ መንገድ ለመሄድ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት በሃሰት መረጃ የሰዎችን ቀልብ በመሳብ እና ክሊክ በማግኘት ይህም ደግሞ የሚያስገኘውን ተራ ጥቅም ብቻ በማየት ለዚህ ዓይነት ርካሽ ሥራ መሠማራት ውርደት ነው። በኢትዮጵያ የሚወጡትን የሐሰት መረጃዎች እያነፈነፈ የሚያጋልጠው Ethiopia Check “ዘሐበሻ” እና “Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ” የተባሉ “በሚዲያ” ስም የሚጠሩ ማክሰኞ … [Read more...] about ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ማጥፋት የሚችል መድኃኒት ተገኘ
የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ውስጥ ሊያጠፋ የሚችል መድኃኒት ማግኘቱን የእጸ ህይወት ጥናትና ምርምር ማዕከል ባለቤት ገልጸዋል። መድኃኒቱን ለማግኘት ለ7 አመታት የፈጀ ምርምር ማድረጋቸውን የማዕከሉ ባለቤት መርጌታ በላይ አዳሙ ተናግረዋል። የእምቦጩ ማጥፊያው በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ሲሆን ለአምስት ዓመት ሳይበላሽ መቆየት እንደሚችል ተገልጿል። የጸረ-እምቦጭ መድኃኒቱ በበጋ ወራት ወይም ዝናባም ባልሆነ ወቅት ቢረጭ ውጤታማ ይሆናል። መድሃኒቱ በአእምሮአዊ ንብረት እውቅና የተሰጠውና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የታየ መሆኑን የፈጠራው ባለቤት ገልጸዋል። አልዓይን አማርኛ … [Read more...] about የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ማጥፋት የሚችል መድኃኒት ተገኘ
አማርኛ ቋንቋ በቻይና መሰጠት ተጀመረ፤ የመጀመሪያው የሕግ መዝገበቃላት በአማርኛ ሊዘጋጅ ነው
ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማኅበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል። በሥነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል። (አል አይን) ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።መዝገበ … [Read more...] about አማርኛ ቋንቋ በቻይና መሰጠት ተጀመረ፤ የመጀመሪያው የሕግ መዝገበቃላት በአማርኛ ሊዘጋጅ ነው
ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”