በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የገንዘብ ኖት ለውጥ ተከትሎ መደናገጥ ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን እያስገባ እንደሆነ ተጠቆመ። ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፤ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ። ጭንቅላቱ የደረቀውና ኪሱ ወደ በመድረቅ ጉዞ ላይ ያለው ህወሓት የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገባ ጎልጉል ያጠናቀረውን መረጃ ለንባብ አብቅቶ ነበር። ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከምኒልክ ቤተመንግሥት የተባረረው ህወሓት መቀሌ በየሆቴሉ መሽጎ በኢትዮጵያ የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህንንም ተግባሩን ለማስፈጸም እንዲረዳው በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ ሐሰተኛ የብር ኖቶች በማተም ተግባር፤ በኮንትሮባንድ ንግድ፤ ገንዘብ ከአገር በማሸሽ፤ ወዘተ ሕገወጥ ተግባራት … [Read more...] about ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው