• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት ወደ አገር በሚገቡ መንገደኞች ገንዘብ ለማስገባት እየጣረ ነው

September 23, 2020 02:00 am by Editor 6 Comments

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የገንዘብ ኖት ለውጥ ተከትሎ መደናገጥ ውስጥ የሚገኘው ህወሓት ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የብር ኖቶችን እያስገባ እንደሆነ ተጠቆመ። ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፤ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠየቀ።

ጭንቅላቱ የደረቀውና ኪሱ ወደ በመድረቅ ጉዞ ላይ ያለው ህወሓት የገንዘብ ለውጡን ተከትሎ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ እንደገባ ጎልጉል ያጠናቀረውን መረጃ ለንባብ አብቅቶ ነበር።

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከምኒልክ ቤተመንግሥት የተባረረው ህወሓት መቀሌ በየሆቴሉ መሽጎ በኢትዮጵያ የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህንንም ተግባሩን ለማስፈጸም እንዲረዳው በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ ሐሰተኛ የብር ኖቶች በማተም ተግባር፤ በኮንትሮባንድ ንግድ፤ ገንዘብ ከአገር በማሸሽ፤ ወዘተ ሕገወጥ ተግባራት ተሰማርቶ አገር የማፍረስ ሥራውን በትጋት ሲሠራ ቆይቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጎልጉል የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ህወሓት እጅግ በርካታ የብር ኖቶችን ከአገር በማውጣት በአሜሪካና በአውሮጳ በሚገኙ አባልና ተላላኪዎቹ እጅ አስቀምጧል። ይህንን መጠኑ እጅግ በርካታ የሆነ ብር ከገንዘብ ምንዛሪ ጀምሮ ለተለያዩ አገር የማፍረስ ተግባራት ወደ አገር በመላክ ሲጠቀምበት እንደነበር መረጃው ይጠቁማል።

የብር ኖቶች መለወጣቸውን ተከትሎ በተሰጠው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ እንደተናገሩት እጅግ በርካታ ገንዘብ በውጭ አገራት በተለይም በጎረቤት አገራት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ጎልጉል ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በህወሓት እጅ በአውሮጳና አሜሪካ የሚገኘው ብር በየጊዜው ለተለያዩ የኮንትሮባንድና የሽብር ሥራ በጎረቤት አገራት በኩል ሲገባ እንደነበር ነው። ሆኖም የገንዘብ ኖት በመቀየሩ ይህ በምዕራቡ ዓለም የተከማቸውን ብር ለመቀየር የህወሓት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ መንገደኞችን እያግባቡ እንደሆነ ጥያቄው የቀረበላቸው ለጎልጉል ተናግረዋል።

ከአሜሪካ ደለስ ኤርፖርት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎችን በመምረጥና ቀረብ ብሎ በማናገር ይህንን ያህል መቶ ሺህ ብር ይዛችሁልን ሂዱ ይህንን ያህል ዶላር እከፍላለን በማለት የማግባባት ጥያቄ እንደቀረበላቸው መረጃ አቀባያችን ተናግረዋል።

ተመሳሳይ ተግባር ከአውሮጳ ለሚነሱ መንገደኞች እየቀረበላቸው እንደሆነ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወገኖች መንግሥት በድንበር በኩል ብቻ ይገባል ብሎ የሚጠብቀው ብር ባልተጠበቀ ሁኔታ በቦሌ በኩል በሻንጣ እየተሞላ እየገባ የመሆኑን ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ይህንን በርካታ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገቡት ሰዎች በጥንቃቄ የተመረጡ የማይጠረጠሩ መንገደኞች፤ የዕድሜ ባለጸጋዎች፤ በተለይም ሴቶች እንደሆኑና በሁሉም መስክ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮጵላን ማረፊያ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

ያለፈው ሳምንት ከዋሽንግተን ደለስ ኤርፖርት ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ከነበረ መንገደኛ የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪዎች የተያዘው ገንዘብ 98,762 ዶላር መያዛቸው ይታወሳል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ        

Filed Under: Left Column, News Tagged With: dulles airport, Ethiopia, new birr notes, new currency, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tariku says

    September 24, 2020 01:56 am at 1:56 am

    በተለያየ አጋጣሚ ውጭም ይሁን ሃገር ውስጥ ያለ ገንዘብ ሲንቀሳቀስና ሲያዝም፡እየታየ ነው ገና ብዙ ነገር ልታይም ይችላል ከዝህ በኋላም በተለያየ አከባቢ የሚነሱ የሽብር ጥቃቶች በተወሰነ መልኩ ሊቆሙ ይችላሉ

    Reply
  2. Kibrey says

    September 24, 2020 09:53 am at 9:53 am

    Ere afh molteh wshet le hzbu stakerb berash mafer alebh yemr

    Reply
  3. TD says

    September 24, 2020 10:09 am at 10:09 am

    Too sad!
    Can’t lead a country by Tit-for-tat principals.

    Reply
  4. Samuel says

    September 24, 2020 09:11 pm at 9:11 pm

    ዶር አብይም እንደ ሕወሀት ሳይደነፋ በብልሀት ብቻ ገና ልክ ያስገባቼዋል እኝህ ሌባ የሌባ ዘር

    Reply
  5. shamsu suliman says

    September 25, 2020 03:39 am at 3:39 am

    ድቡን የአለ ዉሸት

    Reply
  6. A. Belayneh says

    September 25, 2020 06:48 pm at 6:48 pm

    TPLF has mastered the “art” of theft using all available tools. If Eritrea’s experience following separation from Ethiopia is any lesson, TPLF would sink in VERY DEEP hole, and can be expected to do anything and everything to come out of the shit hole. Economic strangulation is an obvious tool available to the federal government, and should use it starting immediately. Forget about the ‘common people’ because most of those are supporters and/or members of TPLF.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule