በሰበታ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ የተከማቸ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ተያዙ።
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የተያዘው ገንዘብ 3 ሚሊየን 751 ሺህ 830 የኢትዮጵያ ብር፣ 2 ሺህ 950 የአሜሪካ ዶላር እና የዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ የፓኪስታንና የኦማን ገንዘቦች ናቸው።
በከተማው የ3ኛ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታደሰ ሁሪሳ ገንዘቡ በግለሰብ ቤት ውስጥ አልጋ ስር ተከማችቶ የተያዘው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅር ክትትል ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ወደ ፊትም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ተናግረዋል።
ገንዘቡ የተያዘው አንድ ፓኪስታናዊ ተከራይቶ በሚኖርበት የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነውም ብለዋል ኃላፊው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply