በጋምቤላ ክልል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ብር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ። ከሚዛን አማን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ህገ ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ከሚዛን አማን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ተሻግሮ ዲማ በተሰኘው ወረዳ ውስጥ በህገወጥ መንግድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሁለት ሚሊየን 490 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጋምቤላ ክልል አስታውቋል። ገንዘቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በህገ ወጥ መልኩ ከሚዛን አማን ተሻግሮ በጋምቤላ ክልል በሚገኘው ዲማ ወረዳ ላይ የክልሉ ፀጥታ አካላትና የመከላከያ ሰራዊት ባደረጉት ጥበቃ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ በአማካኝ በቀን ከ16 ሺህ 700 … [Read more...] about በጋምቤላ 2.5 ሚሊዮን ሕገወጥ ብር ተያዘ
Archives for September 2020
“አልሲሲ የፈጣሪ ጠላት ነው፤ አገራችንን ለቅቀህ ውጣ” የተቃውሞ ሰልፈኞች
በግብጹ ፕሬዘዳንት አልሲሲ ላይ የተነሳው ቁጣ በመላው ግብፅ ተቀጣጥሏል፤ የአልሲሲን አገዛዝ ተቃውመው የሚደረጉ ሰልፎች በመላው ግብፅ መደረጋቸውን ቀጥለዋል። የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ በግብፅ አለመረጋጋትና ትርምስ ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ ይሻላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ተቃዋሚዎች አልሲሲ ስልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ እንደ ዋና ምክያት የሚያነሱት ደግሞ ሙሰኝነታቸውን ነው። ሲሲ ለአመታት ከጦር ኃይሉ ጋር በመሆን ለፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና ጓደኞች ይሆኑ ዘንድ ከተገነቡ ቅንጡ ቤቶችና ከሌሎች በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል እያሉ ነው። ተቃውሞው ቁጣቸው እየጨመረ በሚመጣ አመፀኞች ተቀጣጥሏል። በተለይ በገጠርና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች በርትቷል። ህገ ወጥ ግንባታዎች ይቁሙ … [Read more...] about “አልሲሲ የፈጣሪ ጠላት ነው፤ አገራችንን ለቅቀህ ውጣ” የተቃውሞ ሰልፈኞች
ለኮፍያና ለባጅ ከ415 ሺህ ዶላር በላይ ከባንክ መውሰዱን ዋልታ አመነ
“ከ69 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከመመሪያ ውጪ ከኢትዮጵያ ባንክ መባከኑ በሰነድ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀድሞ ፕሬዝደንት አቶ ባጫ ጊና የተፈረመበትን ሰነድ ዋቢ አድርጎ ባሰናዳው ወሬ በ2010 ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጪ በትንሹ ከ69 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰጠቱን ሸገር 102.1 በመጥቀስ ዘግበን ነበር፡፡ በዚሁ ዓመት በግንቦት ወር መመሪያው የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ ከተፈቀደላቸው የሥራ ዘርፎች ውጪ ላሉ ወይም መመሪያው ለማይመለከታቸው 5 ድርጅቶች በድምሩ 11 ሚሊዮን 841,583 የአሜሪካ ዶላር እንደተሰጠ ከተገኘው ሰነድ በመጥቀስ በዘገባው ተመልክቷል፡፡ በዚሁ ሰነድ ላይ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 500,000 የአሜሪካ ዶላር እንደተፈቀደለት ተጽፏል፡፡ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ለሸገር በላከው ማስተባበያ የውጭ ምንዛሬው የተሰጠኝ ሕጋዊ … [Read more...] about ለኮፍያና ለባጅ ከ415 ሺህ ዶላር በላይ ከባንክ መውሰዱን ዋልታ አመነ
ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ
የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ። የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል። ከመስከረም … [Read more...] about ከመስከረም 25 በኋላ “መንግሥት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ – የፌዴራል ፖሊስ
ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
የጦር መሳሪያ ጨምሮ ሌሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዚህም፡- 18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ደረቅ ጫት፣ እህል፣ ትምባሆ እና ሌሎች ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ እና መቅረጫ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 13 ሚሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለውና 8,980 ኪ.ግ መጠን እንዳለው የተገለጸው ደረቅ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሲጓጓዝ የተያዘ ነው፡፡ ከሱማሌላንድ ወደ ጅጅጋ ሊገቡ የነበሩ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቀብሪበያህ በኩል በኤፌሳር እና ሚኒባስ ተጭኖ ሊገባ የነበረ የውጭ ሀገር ማሽላ እና ዘይት 3,500,000 ብር አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለደቡብ ሱዳን … [Read more...] about ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ!
በፖለቲካ ፓርቲና አክቲቪስት ጫጫታ የሠራዊቱ ተልዕኮው አይደናቀፍም፤ እርምጃ እንወስዳለን–ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ
ሕገ-መንግሥቱን በጣሰ መልኩ በኃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ በሚል ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ በኢፌዴሪ መከላከያ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹምና የኦፕሬሽናል ጉዳዮች ኃላፊ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ። የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየርን ተከትሎ ሠራዊቱ በህገ-ወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ሲውል የነበረው የአብዮታዊ ሠራዊት መገንቢያ ሰነድ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ እንዳላደረገው ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታውሰዋል። ስለሆነም በአገራዊ ሪፎርሙ አዲስ የሠራዊት መገንቢያ ሰነድ አገልግሎት ላይ መዋሉን ጠቁመው÷ አሁን ላይ ሰራዊቱ ያለ ምንም ፖለቲካ ወገንተኝነት ህዝብንና ሀገርን ህልውና እየጠበቀ ይገኛል … [Read more...] about በፖለቲካ ፓርቲና አክቲቪስት ጫጫታ የሠራዊቱ ተልዕኮው አይደናቀፍም፤ እርምጃ እንወስዳለን–ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ
የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በዓላት ያለ ችግር እንዲከበሩ በዘመናዊ መልኩ ተዘጋጅተዋል
መጪዎቹን የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ለማድረግ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶች ማድረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለጸው ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለፀጥታና ደህንነት አካላት በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ተግባራዊ የፀረ-ሽብር ሥልጠና ሰጥቷል። ሥልጠናው ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ ከሪፐብሊካን ጋርድና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ልዩ ኃይል ለተውጣጡ ከ330 በላይ አመራሮችና አባላት ነው የተሰጠው። የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሥልጠናው ሽብርተኝነትን መከላከልና ማክሸፍ፤ የሽብር ተልዕኮዎችንም አስቀድሞ ማወቅ የሚቻልበትን የመረጃ ሥራ ያካተተ ነው። በዚሁ መሰረት ሰልጣኞቹ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊ /ቪ.አይ.ፒ/ እገታን በተቀናጀና … [Read more...] about የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በዓላት ያለ ችግር እንዲከበሩ በዘመናዊ መልኩ ተዘጋጅተዋል
መነሻው ከትግራይ የሆነ 180 ሺህ ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት ንብ ባንክ ሊቀየር ሲል ተያዘ
ከ180 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ ገንዘብ ኖቶችን ወደ ንብ ባንክ ወስደው ሊቀይሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሁለቱ ግለሰቦች በሕጋዊ ባንክ ስም ተመሳስሎ በተሰራ እና ወደፊት በሚጣራ ቲተር በመጠቀም ከ180 ሺህ ብር በላይ ሃሰተኛ ገንዘብ ወደ ንብ ባንክ ወስደው ሊቀይሩ ሲሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ግለሰቦቹ የያዙትን ሃሰተኛ ብር ንብ ባንክ ካዛንቺስ ቅርጫፍ ካሉ ሰራተኞች ጋር 40 ከመቶ ለባንክ 60 ከመቶ ለራሳቸው ለማዋል ስምምነት አድርገው ከመኪናቸው አወጥተው ብሩን ሊመነዝሩ ሲሉ በባንኩ ጥቆማ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይንስና ንግድ ነክ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ጋር በተደረገ … [Read more...] about መነሻው ከትግራይ የሆነ 180 ሺህ ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት ንብ ባንክ ሊቀየር ሲል ተያዘ
አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ
አዲስ አበባ በራሷ ግዛተ-መሬት ላይ የፌዴራል አድያምነት /ክልልነት/ መደራጀት በተመለከተ ባልደራስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት ለፓርቲዎች ጥያቄ አቅርቧል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ትላንት ባወጣው ደብዳቤ እንደጠየቀው የአዲስ አበባን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ታሪካዊ ጉዞ እንዲሳተፉ ለ10 ፓርቲዎች ጥሪውን አቅርቧል። ይህ ባልደራስ ለብልጽግና፤ ለመኢአድ፤ ለኢዜማ፤ ለአብን፤ ለመድረክ፤ ለአረና፤ ለትዴፓ፤ ለኦብነግ እና ሌሎች ፓርቲዎች ባቀረበው ጥሪ ፓርቲዎቹ መስከረም 20፤ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ለሚደረገው ውይይት ፓርቲያቸውን የሚወክሉ 3 አመራሮችን እንዲልኩ ጥሪ አድርጓል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አዲስ አበባ በክልልነት እንድትደራጅ ባልደራስ የፓርቲዎችን ድጋፍ ጠየቀ
ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት እነ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት የክስ ፋይላቸው መቀየሩ ተዘግቦ ነበር። የዚያን ዕለት የቀረበባቸውም ክስ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በአማራ ብሔር ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና የትስስር ድረ ገጾችን በመጠቀምና በአካል በመገኘት፣ በተገለጸው አግባብ ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የ13 ሰው ሕይወት እንዲያልፍና 48,026,526 ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል፣ በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የ167 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ፣ 360 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና 4,673,031,142 ብር ግምት ያለው ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን በመጥቀስ ነበር ዐቃቤ ሕግ ክሱን … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ