በጋምቤላ ክልል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ብር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ።
ከሚዛን አማን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ህገ ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
ከሚዛን አማን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ተሻግሮ ዲማ በተሰኘው ወረዳ ውስጥ በህገወጥ መንግድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ሁለት ሚሊየን 490 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጋምቤላ ክልል አስታውቋል።
ገንዘቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በህገ ወጥ መልኩ ከሚዛን አማን ተሻግሮ በጋምቤላ ክልል በሚገኘው ዲማ ወረዳ ላይ የክልሉ ፀጥታ አካላትና የመከላከያ ሰራዊት ባደረጉት ጥበቃ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ በአማካኝ በቀን ከ16 ሺህ 700 በላይ ሰዎች አዲስ የሒሳብ ደብተር እንደሚከፍቱ አስታውቋል።
በየእለቱም በአማካኝ ከ351 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ንግድ ባንኩ ገቢ እንደሚሆንም ገልጿል። (የውልሰው ገዝሙ) (ፎቶው የተገኘው ገንዘብ ሳይሆን ማሳያ ነው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply