“ከ69 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከመመሪያ ውጪ ከኢትዮጵያ ባንክ መባከኑ በሰነድ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀድሞ ፕሬዝደንት አቶ ባጫ ጊና የተፈረመበትን ሰነድ ዋቢ አድርጎ ባሰናዳው ወሬ በ2010 ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጪ በትንሹ ከ69 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰጠቱን ሸገር 102.1 በመጥቀስ ዘግበን ነበር፡፡ በዚሁ ዓመት በግንቦት ወር መመሪያው የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ ከተፈቀደላቸው የሥራ ዘርፎች ውጪ ላሉ ወይም መመሪያው ለማይመለከታቸው 5 ድርጅቶች በድምሩ 11 ሚሊዮን 841,583 የአሜሪካ ዶላር እንደተሰጠ ከተገኘው ሰነድ በመጥቀስ በዘገባው ተመልክቷል፡፡ በዚሁ ሰነድ ላይ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል 500,000 የአሜሪካ ዶላር እንደተፈቀደለት ተጽፏል፡፡ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ለሸገር በላከው ማስተባበያ የውጭ ምንዛሬው የተሰጠኝ ሕጋዊ … [Read more...] about ለኮፍያና ለባጅ ከ415 ሺህ ዶላር በላይ ከባንክ መውሰዱን ዋልታ አመነ