የትኛው ኦነግ ስለየትኛው ኦነግ መግለጫም ይሁን ተቃውሞ እንደሚሰጥ ግራ እስኪያጋባ የደረሰው ዕድሜ ጠገቡ ኦነግ ተከፋፍሎ አላልቅ ብሎ አሁን ደግሞ አንዱ በአንዱ ላይ ዕርምጃ እወስዳለሁ እያለ ነው። ኢትዮ ኤፍ ኤም ያጠናከረው ዘገባ እንዲህ ይነበባል። ኦነግ ከፖርቲው ህግና ስርአት ባፈነገጠ መልኩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን አሳሳች መግለጫዎችን ሲሰጡ በነበሩ አመራሮቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ። የኦነግ ቃላ አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ አላስፈላጊ መግለጫዎችንና መልዕክት በማስተላለፋቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ላይ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በአመራሮች መካከል የርዕዮተ አለም ልዩነት እንዳለ … [Read more...] about ኦነግ በኦነግ ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ነው
Archives for September 2020
“ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ
ስለ አዲስ አበባ ፍትኅ የሚጠይቅ የማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች ዘመቻ ዛሬ በዋናነት በትዊተር ላይ ተጀመረ። ዘመቻው ዛሬም እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ የገለጡ ሲኾን፦ “በአዲስ አበባ የታየውን የመሬትና የኮንዶምንየም ምዝበራ በመቃወም” ፍትኅ ለመጠየቅ የተጀመረ መኾኑንም አክለዋል። በዘመቻዉ ላይ “#ፍትህለአዲስአበባ”፤ “#አዲስአበባ” እንዲሁም “#ኢትዮጵያ” የሚሉ አሰባሳቢ ቃላት (ሐሽታጎች) ጥቅም ላይ ውለዋል። የዘመቻው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ “ተፈጸመ” ያሉትን አድሏዊ አሠራር እና በደል በመዘርዘር ተቃውሟቸውን እና ቅሬታቸውን ሲያስተጋቡ ተስተውለዋል። የዘመቻው አስተባባሪዎች ባሰራጩት ጽሑፍ፦ “በኢ/ር ታከለ ኡማ አስተዳደር ዘመን በአዲስ አበባ የታለያዩ አድሎአዊ አሠራሮች፤ ጥቅመኝነት፤ የህዝብን ሃብት ማባከን የመሳሰሰሉ ጥፋቶች ተስተውለዋል” ብለዋል። ግድፈቶች … [Read more...] about “ፍትኅ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል የማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ተጀመረ
አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
ሽመልስ አብዲሣ በድብቅ የተናገረውና ለዓላማቸው ሲሉ በቅርቡ አፈትልኮ እንዲወጣ ያደረጉ ወገኖች በለቀቁት መረጃ አዲስ አበባን አስመልክቶ ሽመልስ ይህንን ብሎ ነበር፤ “አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ “አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። “ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን። “ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ … [Read more...] about አዲስ አበባን “irrelevant” በማድረግ ሥራ የሽመልስና የታከለ መናበብ
ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በአቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ ተማም በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ፤ ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ከሚገኙ እና ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እንደነበር ጠቅሷል። ሁለቱ ተከሳሾች “በኃይል፣ በዛቻ፣ በአድማ ወይም ህገ ወጥ በማናቸውም መንገድ በሕገ መንግስቱ የተቋቋመውን ስርዓት ለማፍረስ በማሰብ ከሰኔ 2012 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የስልጣን ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መንግስት ሆኖ … [Read more...] about ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!
ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጥያቄዎቿን እንዲቀበላት ጠየቀች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚነገረው “በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ” ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይሆኑ፣ የተሳሳቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ትርክቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ በተቀነባበረና በተደራጀ ሥልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የማፅዳት እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ቤተ ክህነት ገለጸች። የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊው ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች በስድስት ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ 25 ወረዳዎች በሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የገለጸችው ቤተ ክህነት፣ በጥቅምት ወርና በጥር ወር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሃጫሉ ሞት ምክንያት በአቢያተ ክርስቲያናትና … [Read more...] about ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው
ወደ ዛምቢያ ከተሰደዱ 50 ኢትዮጵያውያን አንዱ ግድያ ተፈጸመበት
ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ዛምቢያ ካቴቴ አውራጃ ውስጥ በበሀገሬው ቺቦላያ ነዋሪዎች በተፈጸመ ጥቃት መገደሉን ዛምቢያ ሪፖርትስ ትናንት በድረ-ገጹ ዘግቧል። አምሳዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዛምቢያ የገቡት ምዋሚ በተሰኘው ድንበር በኩል ሲኾን፤ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከማቅናታቸው አስቀድሞ ካቴቴ ውስጥ በሕገወጥ ቆይተዋል ሲል የአካባቢው ፖሊስ ተናግሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ባረፉበት ቦታ በሌሊት በድንገት ባደረሱት ጥቃት ከግድያው ባሻገር ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን መጠነኛ የመቊሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የአካባቢው ፖሊስ ኮሚሽነር ሉክሰን ሳካላ ገልጠዋል። ከኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ መካከል 38ቱ በፖሊስ ሲያዙ ማንነታቸው ያልተገለጡ ኹለት ስደተኞች ግን ማምለጣቸውን የፖሊስ ኃላፊው አክለው ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዡ፦ የአካባቢው ነዋሪ በሰፈራቸው ስለመጡ ሰዎች ጥርጣሬ … [Read more...] about ወደ ዛምቢያ ከተሰደዱ 50 ኢትዮጵያውያን አንዱ ግድያ ተፈጸመበት
ለኢዜማ ሕገወጥ የመሬት ወረራና ኮንዶ ክፍፍል ዘገባ የታከለ ዑማ ምላሽ
በቅርቡ እንደተሾሙት አዳነች አቤቤ በምርጫ ሳይሆን ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተለወጠ ሕግ በሥልጣን የነበሩት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ በትላንትናው ዕለት ኢዜማ በአዲስ አበባ በርሳቸው አስተዳደር ዘመን ሲካሄድ የቆየውን የመሬት ወረራና ሕገወጥ የኮንዶ ክፍፍል አስመልክቶ ላወጣው ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል። "ሀሰተኛ መረጃ ሀገር ማፍረስ ይቻል ይሆናል እንጂ ሀገር አይገነባም" በሚል ርዕስ አቶ ታከለ በማኅበራዊ ገጻቸው ይህንን ብለዋል። "የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው። "ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛል። "በተለያዩ ጊዜዎች የወሰድናቸው … [Read more...] about ለኢዜማ ሕገወጥ የመሬት ወረራና ኮንዶ ክፍፍል ዘገባ የታከለ ዑማ ምላሽ
“የኃይለሥላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገ(ሩ)…ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል” አቶ ሙሳ
በዱሮ አስተሳሰብ እየኖሩ በአዲሱ ኃይል ጉልበት፤ ዕጣ ፋንታ፤ የወደፊት ራዕይ ላይ በመጫወት መስዋዕትነት የሚያስከፍሉት ፖለቲከኞች ጡረታ መውጣት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አደም ገለጹ። የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሙሳ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ የዓለም ፖለቲካ በጣም ተለዋዋጭ ነው። ትናንት የነበረው የፖለቲካ አረዳድ ዛሬ አይሠራም፤ የለምም። በእኛ አገር ፖለቲካ ትናንት የሁልጊዜ ውሎ ነው። ገና ኃይለስላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገረ ፖለቲከኛ ይዘን ቀጥለናል። ይህ ሁኔታ አገርን ስለማያሻግር እነዚህ ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል። በምትኩ የሚሠራ ኃይል ወንበሩን መረከብ አለበት። እነዚህ አካላት በጊዜያቸው ወቅቱ የሚጠይቀውን መንገድ ሂደው ብዙ ሠርተዋል፤ ለአገርም ያበረከቱት ነገር አለ። … [Read more...] about “የኃይለሥላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገ(ሩ)…ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል” አቶ ሙሳ