• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ደጀኔ ጣፋ፥ ከ “ተጠርጣሪ” ወደ “ተከሳሽ”!

September 1, 2020 03:52 pm by Editor Leave a Comment

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ተከሰሱ። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በአቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ ተማም በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ባቀረበው ክስ፤ ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ከሚገኙ እና ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እንደነበር ጠቅሷል። ሁለቱ ተከሳሾች “በኃይል፣ በዛቻ፣ በአድማ ወይም ህገ ወጥ በማናቸውም መንገድ በሕገ መንግስቱ የተቋቋመውን ስርዓት ለማፍረስ በማሰብ ከሰኔ 2012 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የስልጣን ዘመኑ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መንግስት ሆኖ መቀጠል ስለማይችል የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ግፊት ሲያደርጉ ነበር” ሲል አቃቤ ህግ በክስ ቻርጁ ላይ አስፍሯል።

ተከሳሾቹ “ ‘የኦሮሞ ህዝብ በአመጽ በአንድ ላይ በመነሳት የሀገር ባለቤትነቱን ማረጋገጥ አለበት፣ በሀገሪቱ የሚገኙ የምኒልክ እና ሌሎች ተመሳሳይ ሀውልቶች መፍረስ አለባቸው፣ የኦሮሞ ቄሮዎች የሌሎች ብሔር ተወላጆችን ንብረት ማቃጠል አለባቸው፣ በቄሮ ደም ቤተመንግስት የገባውን ኃይል በቄሮ ትግል ማስወገድ አለብን’ በማለት ህዝብን ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል” ሲል የክስ ሰነዱ አትቷል። ተከሳሾቹ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ያሰቡትን አላማ ለማሳካት መንቀሳቀሳቸውንም አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።

የሃጫሉ የቀብር ስነ ስርዓት በአምቦ እንዲከናወን አስክሬኑ በመሸኘት ላይ እያለ በአንደኛ ተከሳሽነት በክስ መዝገቡ የሰፈሩት አቶ ደጀኔ፤ በተመሳሳይ የምርመራ መዝገብ ተጠርጣሪ ከሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በስልክ ትዕዛዝ መቀበላቸውን የክስ ሰነዱ ያመለክታል። የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ለሌላኛው የፓርቲያቸው አመራራ አቶ ደጀኔ ሰጡት የተባለው ትዕዛዝ “ወጣቶችን አደራጅተው የሃጫሉ አስክሬን ከኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን፣ ቡራዩ ከተማ፣ ኬላ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ እንዳያልፍ እና ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ እንዲያደርጉ” የሚያሳስብ እንደሆነ የክስ ሰነዱ ያብራራል።

አቶ ደጀኔ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው በቡራዩ ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በርካታ ወጣቶችን በማስተባበር መንገድ በማዘጋት እና ከሟች ቤተሰብ ፍቃድ ውጪ የሃጫሉን አስክሬን በማስገደድ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ማድረጋቸውን በክስ ሰነዱ ላይ ተቀምጧል። ተከሳሾቹ ከአቶ በቀለ እና ከሌሎችም ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ያስተባበሯቸው ወጣቶች ጉዳት ለማድረስ የሚያስችሉ የተለያዩ መሳሪያዎችን የያዙ እንደነበርም ክሱ አመልክቷል።

የኦፌኮ ምክትል ዋና ጸሀፊ ድምጻዊ ሃጫሉ በተገደለበት ሰኔ 22፤ 2012 ለሊት፤ አምስት ሰዓት ከ10 ደቂቃ ገደማ በስልክ ሰጡት የተባለው ትዕዛዝም በክስ ሰነዱ ተጠቅሶባቸዋል። አቶ ደጀኔ የስልክ ትዕዛዙን ያስተላለፉት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ደምበል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ለነበረ ግብረአበራቸው መሆኑን አቃቤ ህግ በክሱ አስፍሯል።

እስካሁንም በቁጥጥር ስር አለመዋሉ በሰነዱ የተገለጸው ይህ ግለሰብ፤ የሃጫሉን ግድያ በመቃወም “ወደ መንገድ መውጣታቸውን እና መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድ የመጨረሻ ትግል እንደሚያደርጉ” ለአንደኛ ተከሳሽ ነግሯቸዋል ተብሏል። በስልክ ልውውጡ ወቅት አቶ ደጀኔ ግለሰቡን “በርቱ” ማለታቸውን እና “ሀገሪቷ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጉ እንዲያደርጉ” ትዕዛዝ መስጠታቸውን አቃቤ ህግ በክሱ አትቷል።

ተከሳሹ ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ ማግስት፤ ሰኔ 23፤ 2012፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ አካባቢ ለነበረ ግብረአበራቸውም ሌላ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውም በክስ ሰነዱ ላይ ተቀምጧል። ለጊዜው ስሙ አለመታወቁ በሰነዱ ለተጠቀሰው ግብረአበር የተሰጠው ትዕዛዝ “ወጣቶች ተቀናጅተው በየአካባቢው የመንግስትን መዋቅር እንዲቆጣጠሩ” የሚል እንደነበር አቃቤ ህግ በክሱ ገልጿል።

በተከሳሾቹ በተነሳሳው “ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን የመናድ ተግባር በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ የተለያዩ ንብረቶች መውደማቸውን የአቃቤ ህግ ክስ ዘርዝሯል። አቃቤ ህግ በዚህ የወንጀል ተግባር ምክንያት ተነሳ ባለው ግጭት፤ በቡራዩ ከተማ የ2 ሰዎች እና በአዲስ አበበ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የስድስት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ብሏል።

አቶ ደጀኔ እና አቶ መስተዋርድ በተከሰሱበት ወንጀል “በህዝብ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ቀውስ የደረሰ በመሆኑ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት በሕገ መንግስትና በሕገ መንግስት ስርዓት ላይ በሚደረግ ወንጀል ተከሰዋል” ሲል አቃቤ ህግ በክስ ሰነዱ አስፍሯል። ተከሳሾቹ በክስ ሰነዱ የተጠቀሰባቸው የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 (2) “ወንጀሉ ሲፈጸም በሕዝብ ደህንነት ወይም ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ደርሶ እንደሆነ፤ አድራጊው በዕድሜ ልክ እስራት ወይም ሞት ይቀጣል” በማለት ይደነግጋል።

በዛሬው የችሎት ውሎ የቀረቡት ሁለቱ ተከሳሾች የክስ ቻርጁ እንደደረሳቸው ጠበቃቸው አቶ ቦሬሳ በየነ ገልጸዋል። “የክስ ቻርጁ የመጀመሪያ ቀን የደረሰን ስለሆነ ክሱን አይተን አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገን ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቀናል” ሲሉ ጠበቃ ቦሬሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በዛሬው ችሎት የተከሳሾች የዋስትና መብት በተመለከተም በችሎት የነበሩ ሶስት ጠበቆች ጥያቄ ማቅረባቸውንም አክለዋል።

የዋስትና መብት ጥያቄ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ጥያቄውን መርምሮ ተገቢውን ብይን ለመስጠት ለከነገ በስቲያ ሐሙስ ነሐሴ 28፤ 2012 ቀጠሮ ሰጥቷል። በሐሙሱ ችሎት፤ በክሱ ላይ በጠበቆች በኩል ለሚቀርበው ምላሽ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሚሰጥም የተከሳሾቹ ጠበቃ ገልጸዋል። (በተስፋለም ወልደየስ፥ Ethiopia Insider)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Right Column Tagged With: chilot, dejene taffa, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule