• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለኢዜማ ሕገወጥ የመሬት ወረራና ኮንዶ ክፍፍል ዘገባ የታከለ ዑማ ምላሽ

September 1, 2020 11:03 am by Editor Leave a Comment

በቅርቡ እንደተሾሙት አዳነች አቤቤ በምርጫ ሳይሆን ለዚሁ ዓላማ ተብሎ በተለወጠ ሕግ በሥልጣን የነበሩት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ በትላንትናው ዕለት ኢዜማ በአዲስ አበባ በርሳቸው አስተዳደር ዘመን ሲካሄድ የቆየውን የመሬት ወረራና ሕገወጥ የኮንዶ ክፍፍል አስመልክቶ ላወጣው ዘገባ ምላሽ ሰጥተዋል። “ሀሰተኛ መረጃ ሀገር ማፍረስ ይቻል ይሆናል እንጂ ሀገር አይገነባም” በሚል ርዕስ አቶ ታከለ በማኅበራዊ ገጻቸው ይህንን ብለዋል።

“የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው።

“ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛል።

“በተለያዩ ጊዜዎች የወሰድናቸው እርምጃዎችም ህያው ምስክሮች ናቸው። እኛ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እርምጃ ስንወስድ የዛሬ ተቺዎች የሰብአዊ መብት ተነካ፣ ዜጎች ተፈናቀሉ ብለው ዘመቻ ከከፈቱብን ውስጥ ነበሩ።

“ለ20ሺህ አርሶአደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በተመለከተም ከአንድ አመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ ነው። በድብቅ የተተገበረም ሳይሆን በመንግስት ሚዲያም በይፋ የተገለፀ ነበር።

“ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ከወደቁ በራሳቸው መሬት ላይ በተሰራ ህንጻ ዘበኛ እና ተሸካሚ ሆነው ከቀሩ 67 ሺህ አባወራዎች መሃል የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺህ ኮንዶሚንየም ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም።

“ከዚህ ውጭ በህገወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም።

“ይህ ሥራችን በተደጋጋሚ በይፋ ስንናገር እንደነበረው የምናፍርበት ሳይሆን የምንኮራበት ነው። በግፍ የተገፋን፣ በግፍ ከመሬቱ የተፈናቀለን አርሶ አደር መካስ ያኮራናል!

“በዙሪያዋ ካሉት አርሶ አደሮች ጋር በፍቅር ተሳስባ የምትኖር የተሰናሰለች ከተማ እንጂ በዙሪያዋ ካሉት ህዝቦች ጋር የተቀያየመች ከተማ እንድትኖር አንሻም ነበርና። ይህ ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት መሆኑንም እንገነዘባለን።

“አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶአደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ያሳዝናል።ነገር ግን በሃሰተኛ እና በተጋነነ መረጃ ጠንካራ መምሰል እንጂ መሆን አይቻልም።

በሀሰተኛ መረጃ ድካማችንና ስራችንን ለማጠልሸት ቢሞከርም ስራችን ይናገራልና ፍርድ የህዝብ ነው!”

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics, Right Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule