• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የኃይለሥላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገ(ሩ)…ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል” አቶ ሙሳ

September 1, 2020 07:44 am by Editor 3 Comments


በዱሮ አስተሳሰብ እየኖሩ በአዲሱ ኃይል ጉልበት፤ ዕጣ ፋንታ፤ የወደፊት ራዕይ ላይ በመጫወት መስዋዕትነት የሚያስከፍሉት ፖለቲከኞች ጡረታ መውጣት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሳ አደም ገለጹ።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሙሳ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ የዓለም ፖለቲካ በጣም ተለዋዋጭ ነው። ትናንት የነበረው የፖለቲካ አረዳድ ዛሬ አይሠራም፤ የለምም። በእኛ አገር ፖለቲካ ትናንት የሁልጊዜ ውሎ ነው። ገና ኃይለስላሴና ምኒልክ ዘመንን ያልተሻገረ ፖለቲከኛ ይዘን ቀጥለናል። ይህ ሁኔታ አገርን ስለማያሻግር እነዚህ ፖለቲከኞች ጡረታ ሊወጡ ይገባል። በምትኩ የሚሠራ ኃይል ወንበሩን መረከብ አለበት።

እነዚህ አካላት በጊዜያቸው ወቅቱ የሚጠይቀውን መንገድ ሂደው ብዙ ሠርተዋል፤ ለአገርም ያበረከቱት ነገር አለ። ይሁንና “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አባባላቸው ዛሬም ቀጥሏል። ይህ ደግሞ ወጣቱን እንዳይሠራና አገሩን እነርሱ በሠሩት ላይ ጨምሮ እንዳያሻግር እንቅፋት ሆነውበታል ብለዋል። ሀገራዊ ፖለቲካውና ፖለቲከኛው እንዲሻሻል ከተፈለገ እነዚህ ዘመናቸው ያበቃ ፖለቲከኞች ለተተኪው ወንበር መለቀቅ እንደሚኖርባቸው አስታውቀዋል።

የቀድሞ ሀገራዊ የፖለቲካ አካሄድ መልካምም መጥፎም ታሪኮች እንደነበሩት የሚያነሱት አቶ ሙሳ፤ በዘመናቸው የነበረው የፖለቲካ አረዳድ ይህንን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋልና አድርገውት አልፈዋል። አገርንም ለዛሬው ትውልድ ሠርተውለታል። ሆኖም ያንን ታሪክ አድርገን እንጂ ኑሯችን አድርገን መቀጠል የለብንም። ታሪኩ እንደ ታሪክነቱ ይነበብ፤ ይታወቅ፤ እውነታውን ሁሉም ይረዳው፤ ነገር ግን በዚያ ታሪክ እንድንኖር ሊፈረድብን አይገባም ብለዋል።

ትውልዱ ነገው እንዲበላሽ መፍቀድ የለበትም የሚሉት ሰብሳቢው፤ ዛሬ ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል። በዛሬው አካሄድ የዛሬው ትውልድ መሠራት አለበት። ነገን እያነሱ ትውልዱን ወደትናንት መውሰዱና ማበጣበጡ አገርን ወደኋላ ከመመለስ አይተናነስም። በተለይ ፖለቲከኛው የትናንቱን ለትናንት በመተው ዛሬ በራሱ መንገድ እንዲሻገር እና ለውጥ እንዲመጣ ለተተኪዎች ቦታውን መልቀቅ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።

አገሪቱ በርከት ያሉ በእውቀት መምራትና መሥራት የሚችሉ ወጣት ፖለቲከኞች አሏት፤ እነዚህን ወደ ሥራ ማስገባት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ የሚገልጹት አቶ ሙሳ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለፉት ዓመታትን የምንኖርበት ሊሆን አይገባምና ተሠርታ ያለቀችውን ኢትዮጵያን እንዲሠሩ ለትውልዱ እንፍቀድ ብለዋል።

የቀደሙት የትናንት ፖለቲከኞች ሌላ ሰው እንዲመጣባቸው አይፈልጉም፤ ወጣት ፖለቲከኛን ማየት ያማቸዋል ያሉት አቶ ሙሳ ፤ ይህ ደግሞ በሀገሪቱ ፖለቲከኛም ሆነ ፖለቲካው እንዳይፈጠር ከማድረጉም በላይ ወጣቱን የእሳት እራት እንጂ ባለተስፋ አላደረጉትም ብለዋል። የመሥራት ባህልን እንዲያዳብር እንዳልረዱትም አመልክተዋል።

እንደ አቶ ሙሳ ገለጻ፤ የተማረና የተመራመረ፤ የተሻለውን ለአገር ለማምጣት የሚጥር፤ ጉልበት ያለው ሯጭ ፖለቲከኛ አገር ያስፈልጋታል። እንደውም “የተማረ ይግደለኝ” እንደሚባለው የአገር ፖለቲካ መፈጠር የሚጀምረው ፖለቲከኛውም ፖለቲካውም በእውቀትና በአዲስ አስተሳሰብ ሲቃኝ ብቻ ነው። ስለሆነም የወቅቱን የፖለቲካ ጽንሰሃሳብ ያልተረዱ ሰዎች እየመሩ ግራ ከሚያጋቡ ጡረታ መውጣቱ ለነሱም ለሀገርም እንደሚበጅ ጠቁመዋል።

ፓርቲ የሚባለውም በዘመድ ተሰባስቦ የሚመሰረት ነው። ይህ ደግሞ አገር ለመምራት ሳይሆን ቤተሰብ ለማስተዳደር ብቻ የሚያስብ የሚያደርገው ተግባር ነው። እናም መሰረታዊ የፓርቲ ቁመና ያለው በሃሳብ ልዕልና የሚያምን ፓርቲ ከሌለ ፖለቲካም ፖለቲከኛም ሊፈጠር አይችልም።

ሁለቱም ያለመኖራቸው መንስኤ ነው አሁን ለአገር ፈተናና ዋጋ ማስከፈል ያበቃው ብለዋል። ፓርቲው እንደ ፓርቲ የሚሠራው ሥራ የለም። ህዝቡም ከፓርቲው የሚጠብቀውን እያገኘ አይደለም። ስለዚህም ህዝብ ከመጠቀም ይልቅ በችግር ውስጥ ተዘፍቆ ዓመታትን ዋጋ እየከፈለ እንዲኖር መደረጉንም አመልክተዋል።

ዘመኑን ያልዋጀ፤ አገርን ከፍ ለማድረግ በማያስችል ጉዳይ ላይ መስዋዕት እየከፈልን ነው የሚሉት አቶ ሙሳ፤ ትውልዱን በማደንቆር የተካኑ ፖለቲከኞች ጡረታ ይውጡና አዳዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብና እውቀቱ ያላቸው አካላት ወንበሩን ይረከቡ ብለዋል።

ሀገራዊ የፖለቲካ አካሂዶች በመርህ፤ በፖሊሲ ላይ የተመሰረቱና ከአገርና ከህዝብ ጥቅም አንጻር የተቃኙ መሆን መቻልም አለባቸው። በዚህ ላይም በስፋት መሥራት መጀመር አለብን ሲሉም ነሐሴ 24፥ 2012 ለታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ “ብሔሬን ውሰዱ ኢትዮጵያን ግን አትንኩ” በሚለው አስደማሚ ንግግራቸው ይታወቃሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews, Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Yefa Bedane says

    September 2, 2020 02:30 am at 2:30 am

    አቶ ሙሳ ይህንን ዘመናዊ አስተሳብክን በነጠረ መልኩ በማስቀመጥህ አክበሮቴና አድናቆቴን እገልጽልሃሉ።አገሪቱ እኮ ወቅቱን በማይመጥን በታሪክ በለሙያተኞች ተጽፎ መቀመጥ ያለበትን ትሪክት እያነሱ ለዛሬው ችግራችን መፍትሄ የማይሆን ይልቁን አገራችንና ህዝቡን በክልል በዘር በጎሳ በቁዋንቀዋ እንዲሁም በሃይማኖት ከፋፍሎ እንዲፈጅ መርዛቸውን በውሰጥና በወጭ እየረጩ ያሉት እነዚህ የሥልጣን ጥማኞችና አዋቂ ከእኛ በላይ ለአሠር ብለወ በህዝቡ ጫንቃ ላይ የተጣበቁ ያረጁ ሰዎች ሊወገዱ ወይም ከመድረኩ ሊነሱ ይገባል።እነሱን ዘወትር በየመድረኩ የተጨመደደ ፊታቸውን ከማየትና ያረጀ ንግግራቸውን ከመስማት የበለጠ የሰለቸን ነገር የለምና።

    Reply
    • Iwunetu Yiwuta says

      September 3, 2020 08:45 pm at 8:45 pm

      It is good to think about the future. When we go forward should we need to forget what has been done yesterday. I don’t think so. When one group is always telling us the history of their kings and other we don’t share with them, how come Musa tells us to forget what these criminals done on our people and take them as our heroes unless these extremist accepts the crimes these kings did to us? Musa can accept and even he can change his ethnic background in favour of unity. But he can tell to others to deny their ethnic background and advocate unity without equality and national consensus.

      Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    September 12, 2020 04:39 am at 4:39 am

    ኣቶ ሙሳ የሚናገሩት፥ ሃቅን ያዘለ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule