የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጥያቄዎቿን እንዲቀበላት ጠየቀች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚነገረው “በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ” ተብለው ብቻ የሚታለፉ ሳይሆኑ፣ የተሳሳቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ትርክቶችንና ጂኦ ፖለቲካዊ ዳራዎችን መነሻ በማድረግ በተቀነባበረና በተደራጀ ሥልት የሚፈጸሙ ኦርቶዶክሳውያንን የማፅዳት እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ቤተ ክህነት ገለጸች። የኦሮምኛ ቋንቋ ድምፃዊው ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ምክንያት በማድረግ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች በስድስት ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ 25 ወረዳዎች በሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የገለጸችው ቤተ ክህነት፣ በጥቅምት ወርና በጥር ወር ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሃጫሉ ሞት ምክንያት በአቢያተ ክርስቲያናትና … [Read more...] about ጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ በኦሮሚያ የተፈጸመው ኦርቶዶክሳውያንን የማጽዳት እንቅስቃሴ ነው