የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሠራር ለውጥ ማድረጉን ተናገረ። እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፦ በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ነግሯል። ይህ አሰራርም ከነገ መስከረም 7፣2013 ይጀመራል ተብሏል። በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል … [Read more...] about ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ንብረትን በስጦታ ማስተላለፍ ታገደ
Archives for September 2020
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ እንደገለጹት፣ በክልሉ በሚገኙ 4 የተለያዩ ኬላዎች በተደረገ ፍተሻ 2,370,000 ብር በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ በክልሉ ኩርሙክ ወረዳ ሱዳን ድንበር አካባቢ በግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 600 ሺህ ብር የሚሆን ገንዘብ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቡ 600 ሺህ ብር በሞተር ብስክሌት ጭኖ ሲጓዝ የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል። በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪው ለፖሊስ በሰጠው ቃል ገንዘቡን ለወርቅ ግዥ እያንቀሳቀስኩ ነው ማለቱን ተናግረዋል። በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ማንኩሽ ኬላ 300 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን … [Read more...] about በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ህገ-ወጥ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 99 ሺህ የሚጠጋ ዶላር ተያዘ
የዛሬ ሳምንት ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ከነበረው መንገደኛ ላይ ዋሽንግተን በሚገኘው ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪዎች የተያዘው ገንዘብ 99 ሺህ ዶላር የሚጠጋ እንደሆነ ተነግሯል። ቢቢሲ እንዳረጋገጠው ከግለሰቡ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠን 98,762 ዶላር ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ3.6 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። የጉምሩክ መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኛ ስቲቭ ሳፕ ለቢቢሲ በሰጡት የጽሁፍ ምላሽ ላይ እንዳመለከቱት፣ ግለሰቡ ይዞት የነበረው ዶላር የተያዘበት ተጓዦች የያዙትን የገንዘብ መጠን እንዲያሳውቁ የሚጠይቀውን የአገሪቱን ሕግ በመተለላፍ ነው። በተጨ ማሪም ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በዚሁ ሳቢያ ያልታሰረ ሲሆን የወንጀል ክስ ስላልተመሰረተበትም ማንነቱ እንደማይገለጽ ለማወቅ … [Read more...] about ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 99 ሺህ የሚጠጋ ዶላር ተያዘ
ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በተከሰሱ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዐቃቤ ህግ ምስክር ማሰማት ጀመረ። በእነ ጌታቸው አሰፋ የክስ መዝገብ በ26 የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በተከሰሱበት በአዋጅ ከተሰጣቸው ስልጣን ውጪ ሰዎችን በመያዝና በማሰር ስልጣንን ያለ አግባብ መገልግል ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው የማይገለፅ ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አጠቃላይ 22 ተከሳሾች ሲሆኑ፥ ጌታቸው አሰፋ፣ አፅበሃ ግደይ፣ አሰፋ በላይ እና ሺሻይ ልኡል በሌሉበት ነው ጉዳያቸው የታየው። ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/ 2003 መሰረት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው እና ማንነታቸው የማይገለፅ 29 ምስክሮችን … [Read more...] about ለጌታቸው አሰፋና መሰሎቹ ክስ ምስክር ማሰማት ተጀመረ
“በጥቁር ገበያ” ምንዛሪ የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ
የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ። በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል። የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው። በኢትዮጵያ ሆቴል እና ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፋቸውን ዛሬ ረፋዱን በቦታው የተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል። በሱቆቹ አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ … [Read more...] about “በጥቁር ገበያ” ምንዛሪ የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ
ጭንቅላቱ የደረቀው ህወሓት ኪሱም ሊደርቅ ነው
የብር ኖቶች መቀየር በህወሓት ሠፈር መደናገጥ ፈጥሯል ኢትዮጵያ በአዳዲስ የብር ኖቶች እንደምትጠቀም ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ይፋ ካደረጉ በኋላ መቀሌ የመሸገው ህወሓት ችግር ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል። አዳዲሶቹ ብሮች ሙስናን እና የኮንትሮባንድን ንግድ መቀልበስ ዓላማው ማድረጉ ተነግሯል። ላለፉት ሁለት ዓመታት መቀሌ መሽጎ የሚገኘው ህወሓት የተባለው የበረኻ ወንበዴዎች ስብስብ ላለፉት እጅግ በርካታ ዓመታት ኢትዮጵያን ያለገደብ ሲዘርፍ የነበረ ቡድን መሆኑን ራሱም የሚመሰክረው ሐቅ ነው። ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ከምኒልክ ቤተመንግሥት ከተባረረ ወዲህ መቀሌ በየሆቴሉ መሽጎ የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህንንም ተግባሩን ለማስፈጸም እንዲረዳው በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ ሐሰተኛ የብር ኖቶች በማተም ተግባር፤ በኮንትሮባንድ ንግድ፤ ገንዘብ ከአገር በማሸሽ፤ ወዘተ ሕገወጥ ተግባራት … [Read more...] about ጭንቅላቱ የደረቀው ህወሓት ኪሱም ሊደርቅ ነው
ሕገወጥና ሃሰተኛ ገንዘቦችን የሚሰበስቡ ባንኮች ይዘጋሉ
ህገ ወጥና ሀሰተኛ ገንዘቦችን በሚሰበስቡ ባንኮች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠነቀቁ፡፡ የኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ መቀየርን በማስመልከት ዛሬ በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንደተናገሩት፤ ከብር ኖቶች መቀየር ጋር በተያያዘ ህገ ወጥና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰበስቡ ባንኮች መኖራቸውን መንግሥት ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ አግኝቷል፡፡ በመሆኑም አዲስ የገንዘብ የብር ኖቶች መቀየራቸውን ተከትሎ መንግሥት ህገ ወጥና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰባስቡ ባንኮች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ መንግሥት የባንኮችን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውዱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ባንኮችም በተለይ አሮጌው ንዘብ በአዲሱ የመቀየር ሥራ ሲሰራ ሀሰተኛና ህገ ወጥ ገንዘቦችን ከመሰብሰብ … [Read more...] about ሕገወጥና ሃሰተኛ ገንዘቦችን የሚሰበስቡ ባንኮች ይዘጋሉ
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ 650 መኪናዎችን አስገባ፤ ለጸጥታ አካላት ዕውቅና ሰጠ
የኦሮሚያ ፖሊስ 650 መኪናዎችን ማስገባቱን እሁድ ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሲዮን ፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ “ለሰላም ተግባር” እንዲውሉ ነው የገቡት የተባለላቸው መኪናዎች የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የፖሊስ ኮሌጁ የሚጠቀሙባቸው መሆኑን ኮሚሲዮኑ ገልጾዋል፡፡ በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት እውቅና ሰጥቷል። በናዝሬት ገልማ በአባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር። የእውቅና ስነስርዓቱ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ፖሊሶች የማዕረግ እድገት መስጠትን የሚጨምር ነበር። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ የክልሉ ፖሊስ አሁን የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ … [Read more...] about የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ 650 መኪናዎችን አስገባ፤ ለጸጥታ አካላት ዕውቅና ሰጠ
ዳውድ ኢብሣ ከህወሓት ጋር በማበርና በሌሎች ምክንያቶች ከሥልጣን ተወገዱ
“ሕወሓት በኦሮሞ ህዝብና ታጋዮች ላይ ላደረሰው ጉዳት ይቅርታ ካልጠየቀ ከፓርቲው ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም” ሲል ኦነግ አስታወቀ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ ድርጅቱን ለ21 ዓመት የመሩትን አቶ ዳውድ ኢብሳን ከሊቀመንበርነት ማንሳቱን ይፋ አድርጓል። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ አቶ ዳዉድ ኢብሳ በሊቀመንበርነት በቆዩባቸው 21 ዓመታት “የድርጅቱን ገንዘብና ሀብት ብቻቸውን ሲያዙበት ኖረዋል ፤ በድርጅቱ ውስጥ አድልዎ በመፍጠር የአካባቢያቸውን ሰዎችና ዘመዶች ቁልፍ የስራ መደቦች ላይ በመመደብ ጥቅማቸውን አስጠብቀዋል” ሲሉ ለአል ዐይን ኒውስ ተናግረዋል። ግንባሩ የሊቀመንበሩን መታገድ በተመለከተ መግለጫም አውጥቷል። መግለጫው አቶ ዳውድን “በዚህ መሰል ኣካሄድ ከድርጅቱ ህገ ደንብና አሰራር ውጭ የራሳቸውን አምባገነንነት በድርጅቱ ላይ … [Read more...] about ዳውድ ኢብሣ ከህወሓት ጋር በማበርና በሌሎች ምክንያቶች ከሥልጣን ተወገዱ
ሶማሌ ክልል የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሊጀምር ነው
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ! ትላንት (እሁድ) ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል። በተጨማሪ ከመንግሥት ጦር መሳሪያ ውጭ፣ ለሲቪል ግለሰቦች ታጥቆ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑንም ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ገልፀዋል ። አክለውም ይህ የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ውሳኔው ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ተብሎ የታወጀ ውሳኔ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል። የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ ያለው የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ዘመቻ በቂ አቅምና ዝግጅትም አላቸው ያሉት … [Read more...] about ሶማሌ ክልል የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሊጀምር ነው