የዛሬ ሳምንት ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ከነበረው መንገደኛ ላይ ዋሽንግተን በሚገኘው ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪዎች የተያዘው ገንዘብ 99 ሺህ ዶላር የሚጠጋ እንደሆነ ተነግሯል። ቢቢሲ እንዳረጋገጠው ከግለሰቡ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠን 98,762 ዶላር ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ3.6 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። የጉምሩክ መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኛ ስቲቭ ሳፕ ለቢቢሲ በሰጡት የጽሁፍ ምላሽ ላይ እንዳመለከቱት፣ ግለሰቡ ይዞት የነበረው ዶላር የተያዘበት ተጓዦች የያዙትን የገንዘብ መጠን እንዲያሳውቁ የሚጠይቀውን የአገሪቱን ሕግ በመተለላፍ ነው። በተጨ ማሪም ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በዚሁ ሳቢያ ያልታሰረ ሲሆን የወንጀል ክስ ስላልተመሰረተበትም ማንነቱ እንደማይገለጽ ለማወቅ … [Read more...] about ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ 99 ሺህ የሚጠጋ ዶላር ተያዘ