የኦሮሚያ ፖሊስ 650 መኪናዎችን ማስገባቱን እሁድ ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሲዮን ፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡ “ለሰላም ተግባር” እንዲውሉ ነው የገቡት የተባለላቸው መኪናዎች የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የፖሊስ ኮሌጁ የሚጠቀሙባቸው መሆኑን ኮሚሲዮኑ ገልጾዋል፡፡
በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት እውቅና ሰጥቷል።
በናዝሬት ገልማ በአባ ገዳ አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
የእውቅና ስነስርዓቱ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ፖሊሶች የማዕረግ እድገት መስጠትን የሚጨምር ነበር።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ የክልሉ ፖሊስ አሁን የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ከመቼው ጊዜ በላቀ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን በስነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply