የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ!
ትላንት (እሁድ) ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል።
በተጨማሪ ከመንግሥት ጦር መሳሪያ ውጭ፣ ለሲቪል ግለሰቦች ታጥቆ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑንም ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ገልፀዋል ።
አክለውም ይህ የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ውሳኔው ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ተብሎ የታወጀ ውሳኔ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል።
የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ ያለው የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ዘመቻ በቂ አቅምና ዝግጅትም አላቸው ያሉት ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ሁሉም የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ህዘቦች ላይ ከማንኛውም የፀጥታ ችግር የመከላከል ግዴታቸውን እንዲወጡና በአንድም የሲቪል ግለሰብ እጅ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳይታይ አሳስበዋል።
በክልሉ ውስጥ በተለይ በማህበረሰቡ ይዞታ ያለውን ጦር መሳሪያዎች በአርብቶና አርሶ አደሩ ማህበረተሰብ መካከል ግጭት በመፍጠር ለዜጎች ኪሳራና የህይወት ማጥፋት አደጋ እንደሚያስከትልም ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ ለሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply