የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ሁለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከህዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ሲከታተሉ ቆይተው፥ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡ ህገ … [Read more...] about በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ
illegal weapon
የትህነግ የጦር መሳሪያ ዝውውር ኮሪደሮቹ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። በአገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በእጅጉ ተንሰራፍቶ ከሚገኙት ሦስት ሕገወጥ ሥራዎች መካከል አንዱ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሐሰተኛ የዜና ዘገባዎች ናቸው። በሦስቱም ውስጥ አሸባሪው ህወሓት እጁ እንዳለበት በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድብቅ ምሥጢራትን በማውጣት የሚታወቀው ethio wiki leaks “ህወሓት እና የጦር መሳሪያ … [Read more...] about የትህነግ የጦር መሳሪያ ዝውውር ኮሪደሮቹ
ወደ ጎንደር ከተማ ሊገባ የነበረ 76 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና 19 ሺህ ጥይት በቁጥጥር ሥር ዋለ
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሳንጃ ከተማ በሁለት ባጃጆች ተጭኖ በድብቅ ወደ ጎንደር ከተማ ሊገባ የነበረ 76 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና 19 ሺህ ጥይት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ሽጉጡና ጥይቱ በቁጥጥር ሥር የዋለው በላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ "ኢትዮጵያ ካርታ" በተባለው ቦታ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ሚዲያ ዋና ክፍል ሃላፊ ኮማንደር እንየው ውብነህ ተናግረዋል። ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ በባጃጆች ተጭኖ ወደ ጎንደር ከተማ ለማስገባት ሲሞከር የፀጥታ ሃይሉ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል። ሽጉጡና ጥይቱ በሰሌዳ ቁጥር 1-25591 እና 1-39321 አ.ማ በሆኑ ሁለት ባለ ሦስት እግር ባጃጆች አማካኝነት ተደብቆ በመጓጓዝ ላይ ሳለ እንደተገኘ ኮማንደሩ ገልጸዋል። ኮማንደር እንየው እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት … [Read more...] about ወደ ጎንደር ከተማ ሊገባ የነበረ 76 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና 19 ሺህ ጥይት በቁጥጥር ሥር ዋለ
ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጋምቤላ ከተማ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጋር ትናንት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ቡን ዌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያው የተገኘው በጋምቤላ ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተጭኖ ለማስተላለፍ ሲሞከር ነው። ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሳሪያ መካከል አንድ ላውንቸር፣ አንድ ክላሽንኮቭ ከ705 ጥይት ጋር እንዲሁም 76 ዲሽቃ እንደሚገኝበት አመልክተዋል። ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ በሰጡት ቃል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊተላለፉ እንደነበር መናገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። የክልሉ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል። … [Read more...] about ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 3 ሺህ 676 የክላሽ ጥይት፣ 1 ሺህ 288 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦችን ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ አስታውቀዋል። እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ ገለጻ በክፍለ ከተማው ብሎም በከተማዋ መሰል ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ ተደጋግመው ቢከሰቱም በፀጥታ ኀይሉ የጠነከረ ትጋትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ። አሸባሪው ህወሓት በየቦታው ህዝብን ለማጥፋት እሳት እያነደደ ባለበት በዚህ ጊዜ መላው ህዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሆን … [Read more...] about በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና የተለያዩ መሳሪያዎች ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣ 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣ 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል። ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥና የተለያዩ መሳሪያዎች ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ህገ-ወጥ ጥይቶቹን በአይሱዙ የጭነት መኪና ሲጓጓዝ በተደረገ ክትትልና ፍተሸ መያዙን በምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአከባቢ ጸጥታና ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር ሳጅን ምትኩ ብርሃኑ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ
ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ሥር የዋሉ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች
መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው። የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲዘዋወር በድንገተኛ ፍተሻ ተይዟል (እንደ ጎንደር ከተማ ፖሊስ መረጃ) በሀመር ወረዳ በዚህ እያጠናቀቅን ባለነው ወር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 መሳሪያ፣ 14 ክላሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን ተይዟል። በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ 10 ባለሰደፍና 10 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎች ተይዘዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 2 … [Read more...] about ባጠናቀቅነው ነሀሴ ወር በቁጥጥር ሥር የዋሉ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች
በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በመንግስት አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል። ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኘው አዋሮ ቆራ አካባቢ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ትናንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው ግለሰቦቹን ከነጥይቶቹ መቆጣጠር የተቻለው ብለዋል። ኮማንደር ሲሳይ እንዳመለከቱት፤ ግለሰቦቹ ጥይቶቹን በሴቶች "ታይት" አልባሳት ጠቅልለው በማዳበሪያ ውስጥ መድሃኒት አስመስለው በመጫን ከቡራዩ ከተማ ወደ አምቦ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው የተደረሰባቸው። በዚህም አሽከርካሪው፣ ፋርማሲስት እና ሁለት የጥይቱ ተቀባዮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ … [Read more...] about በአምቦ ከተማ ጥይቶችን በአምቡላንስ ሲያጓጉዙ የተገኙ ተያዙ
በሲዳማ/ሀዋሳ 128 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፤ 2 መትረየስ ከ8,129 ጥይት ጋር ተያዘ
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ከህብረተሰቡ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲከታተል ቆይቶ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጭኮ ከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ ለገሰ ገልፀዋል፡፡ በጭኮ ከተማ ላይ በተደረገው ክትትል 30 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና ሁለት መትረየስ የተያዘ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ወልደ አማኑኤል ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የፌደራል ፓሊስ እና የክልሉ ልዩ … [Read more...] about በሲዳማ/ሀዋሳ 128 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፤ 2 መትረየስ ከ8,129 ጥይት ጋር ተያዘ