በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ31 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ህገ-ወጥ ጥይቶቹን በአይሱዙ የጭነት መኪና ሲጓጓዝ በተደረገ ክትትልና ፍተሸ መያዙን በምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአከባቢ ጸጥታና ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር ሳጅን ምትኩ ብርሃኑ ገልጸዋል።
ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply