መነሻውን ከጋምቤላ ያደረገ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-15074 አ/አ በሆነ ዶልፊን ህዝብ ማመላለሻ ሲዘዋወር የነበረ ህገወጥ መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በዚህ ወር ተይዟል፤ የተያዘው መሳሪያ በቁጥር 12 ክላሽንኮቭ እና 5 ጥይት መያዣ ነው።
የሰሌዳ ቁጥር A76390 በሆነ ቪትዝ መኪና 5 ክላሽንኮቭ ከ132 ጥይት ጋር ሲዘዋወር በድንገተኛ ፍተሻ ተይዟል (እንደ ጎንደር ከተማ ፖሊስ መረጃ)
በሀመር ወረዳ በዚህ እያጠናቀቅን ባለነው ወር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 10 መሳሪያ፣ 14 ክላሽ ጥይት፣ 3 የክላሽ መጋዘን ተይዟል።
በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አምባሳደር ፔንሲዮን ውስጥ 10 ባለሰደፍና 10 ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች እና 17 የክላሽንኮቭ ጥይት ካርታዎች ተይዘዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 2 ግለሰቦች ተይዘዋል።
በባህር ዳር ከተማ በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ 1 ሺህ 669 የብሬን ጥይት በዚህ ወር ተይዟል።
ከከሚሴ ወደ አ/አ ሊዘዋወር የነበረ 53 ህገወጥ ጩቤ ፣ 30 የጥይት መያዣ ካርታ፣ 30 እንግብ፣ 30 የትጥቅ መያዣ ቀበቶ ሸዋ ሮቢት ላይ ተይዟል።
በገንደውሃ ከተማ አንድ ግለሰብ 30 የክላሽ ካዝናዎችን በህገወጥ መንገድ በኩርሲ ወንበሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዟል።
በከፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በኬላ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 634 ፍሬ የክላሽ ጥይትና 50,055 ብር ከነተጠርጣሪዎቹ ተይዟል።
የመጨረሻ ቀን ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ነጆ ከተማ ላይ 25,335 የክላሽ እና የብሬን ጥይት መያዙን ለኢዜአ ገልጿል።
ይህን ጥይት ከአ/አ ከተማ በ ኮድ 3 A 32684 አይሱዙ መኪና ተጭኖ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ብሎ ለፈረጀው ሸኔ ቡድን እንዲደረሰው የታቀደ ሲሆን ነጆ ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ፖሊስ አምቦ ባቢቻ ላይ 3 ሺህ የክላሽ ጥይት ተይዟል፤ ይህም በተመሳሳይ ለሸኔ ሊሰጥ ነበር የተባለ ሲሆን ጥይቱን ለማድረስ የሞከሩ ግለሰቦችም በፖሊስ ተይዘዋል።
ጥንቃቄ፤ ከላይ የተጠቀሱት የህገወጥ መሳሪያ ዝውውሮች በዚህ ወር ከተሰሙት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ፤ ሌሎች ተዳራሽ ያልሆኑ ሊኖሩ ይችላሉ።@tikvahethiopia
በኩርሲ ወንበሮች ውስጥ የክላሽ ካዝናዎችን ደብቆ የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በኩርሲ ወንበሮች ውስጥ የክላሽ ካዝናዎችን ደብቆ የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን በአማራ ክልል የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ግለሰቡ 30 የክላሽ ካዝናዎችን በሕገወጥ መንገድ ይዞ ሲንቀሳቀስ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማ በሕዝብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፖሊስ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።
ግለሰቡ ካዝናዎቹን ለንግድ ሥራ ወደ ባሕርዳር ይዞ ለመውጣት መንቀሳቀሱን ገልጿል።
መኖሪያው በባሕርዳር ዙሪያ ወረዳ ዘንዘልማ ቀበሌ የሆነው አቶ አለሙ ታረቀኝ 30 የክላሽ ካዝናዎችን በሶስት የመቀመጫ ኩርሲዎች ውስጥ አስገብቶ አልጋ ወደያዘበት ሆቴል ሲገባ የሆቴሉ ባለቤቶች ባደረጉት ፍተሻ እንደተያዘ ፖሊስ ገልጿል።
ግለሰቡ ያሳየው ከነበረው ባሕርይ በመነሳት ባደረጉት ፍተሻ የኩርሲ ወንበሮቹ ተቀደው ሲታዩ ካዝናዎቹ መገኘታቸው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስታውቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply