በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ከህብረተሰቡ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲከታተል ቆይቶ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጭኮ ከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
በጭኮ ከተማ ላይ በተደረገው ክትትል 30 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና ሁለት መትረየስ የተያዘ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ወልደ አማኑኤል ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የፌደራል ፓሊስ እና የክልሉ ልዩ ሀይል በጋራ ባደረጉት ፍተሻ 98 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ4,583 መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም 3,546 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ ለገሰ ገልፀዋል፡፡ (ኢቢሲ)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ዛሬም ይህንን መሳሪያ የትግራዩ ነፍሰ_ገዳይ የነበረው ህወሃት ከትግራይ በረሃዎች ሆኖ ሕዝብን ለማተራመስ ልኮታል ብላችሁ እንዳታስቁን ፥ የነፍሰ_ገዳዩ አብይ አህመድ አሊ ሥርዓት ከተጀመረ ጀምሮ መሳሪያ በገፍ ይገባል ፥ ሕዝብ በየቀኑ እንደ ቅጠል ይረግፋል ፥ በሀገሪቱ ላይ ሥርዓት አልበኝነት ሰፍኖዋል ፥ ዜጎች በሠላም ወጥተው መግባት አልቻሉም ፥ ንጹሃን ምንም በማያውቁት ነገር ይፈጃሉ ፥ ይታረዳሉ ፥ የሰው ልጅ እንደ እንስሳ ተጋድሞ የታረደው በአብይ አመራር ነው ፥ ትኩስ እመጫት ከእነልጇ የታረደችው በአብይ ሥርዓት ነው ፥ እርግዝ ሴት ሆዷ ተቀዶ ሽሉ እንዲበላ የተደረገው በአብይ ሥርዓት ነው ፥ በዚህ 3ዓመታት ውስጥ ምን ያልተደረገ ጉድ አለ ! ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊ ሃበ እግዚአብሔር @
Wanna ANaa says
This story better be told to the kids, otherwise everyone knows about the sponsor of any crime in the land.