በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣ 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣ 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል።
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply