
በጋምቤላ ከተማ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጋር ትናንት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቡን ዌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያው የተገኘው በጋምቤላ ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተጭኖ ለማስተላለፍ ሲሞከር ነው።
ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሳሪያ መካከል አንድ ላውንቸር፣ አንድ ክላሽንኮቭ ከ705 ጥይት ጋር እንዲሁም 76 ዲሽቃ እንደሚገኝበት አመልክተዋል።
ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ በሰጡት ቃል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊተላለፉ እንደነበር መናገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።
የክልሉ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply