በአፋር ክልል የጭፍራ ወረዳ ፖሊስ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ደብቀው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሁለት ተጠርጠሪዎች መያዙን አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አብደላ ሁመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ትላንት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው። በጭፍራ ከተማ ድንገት በተካሄደ የቤት ለቤት ፍተሻ ግለሰቦቹ ከደበቋቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር መያዘቸውን ተናግረዋል ። በግለሰቦቹ መኖሪያ ቤቶች ተደብቀው ከተያዙ የጦር መሳሪያዎች መካከል አራት ክላሽንኮቨ ጠብመንጃና አራት ሽጉጦች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። (ኢዜአ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በአፋር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በመደበቅ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ
illegal weapon
ሕገወጥ መሣሪያዎችና ተሠርቀው የተከማቹ የመኪና ዕቃዎች ተያዙ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ 53 ሕገወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች ባለፈው እሁድ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ቀሬ ከተማ ኬላ ላይ መያዛቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበባየሁ ገረመው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦችና ሹፌር ያመለጡ በመሆናቸው እነሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አበባየሁ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ በልደታ ክ/ከተማ ተሠርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀልን ለመከላከል የክትትልና … [Read more...] about ሕገወጥ መሣሪያዎችና ተሠርቀው የተከማቹ የመኪና ዕቃዎች ተያዙ
ሶማሌ ክልል የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሊጀምር ነው
የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር አስታወቁ! ትላንት (እሁድ) ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በሁሉም የሶማሌ ክልል አከባቢዎች ጦር መሳሪያዎችን የመሰብሰብ ዘመቻ እንደሚጀመር እና ከአሁን በኋላ ለአንድም የሲቪል ማህበረሰብ ትጥቅ እንደማይፈቀድላቸው አስታወቀዋል። በተጨማሪ ከመንግሥት ጦር መሳሪያ ውጭ፣ ለሲቪል ግለሰቦች ታጥቆ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑንም ዋና አዛዥ መሀመድ አህመድ ገልፀዋል ። አክለውም ይህ የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ውሳኔው ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ተብሎ የታወጀ ውሳኔ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል። የክልሉ ፀጥታ አካላት በክልሉ ውስጥ ያለው የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ዘመቻ በቂ አቅምና ዝግጅትም አላቸው ያሉት … [Read more...] about ሶማሌ ክልል የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሊጀምር ነው
አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። በአገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በእጅጉ ተንሰራፍቶ ከሚገኙት ሦስት ሕገወጥ ሥራዎች መካከል አንዱ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሐሰተኛ የዜና ዘገባዎች ናቸው። በሦስቱም ውስጥ አሸባሪው ህወሓት እጁ እንዳለበት በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድብቅ ምሥጢራትን በማውጣት የሚታወቀው ethio wiki leaks “ህወሓት እና የጦር መሳሪያ … [Read more...] about አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው