በአፋር ክልል የጭፍራ ወረዳ ፖሊስ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ደብቀው አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን ሁለት ተጠርጠሪዎች መያዙን አስታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አብደላ ሁመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ትላንት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው።
በጭፍራ ከተማ ድንገት በተካሄደ የቤት ለቤት ፍተሻ ግለሰቦቹ ከደበቋቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር መያዘቸውን ተናግረዋል ።
በግለሰቦቹ መኖሪያ ቤቶች ተደብቀው ከተያዙ የጦር መሳሪያዎች መካከል አራት ክላሽንኮቨ ጠብመንጃና አራት ሽጉጦች እንደሚገኙበት ተናግረዋል። (ኢዜአ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply