በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ 53 ሕገወጥ ሽጉጦችና 3860 የሽጉጥ ጥይቶች ባለፈው እሁድ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያሉ በጎሃ ቀሬ ከተማ ኬላ ላይ መያዛቸውን የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር አበባየሁ ገረመው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩት ግለሰቦችና ሹፌር ያመለጡ በመሆናቸው እነሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር አበባየሁ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በአዲስ አበባ በልደታ ክ/ከተማ ተሠርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀልን ለመከላከል የክትትልና … [Read more...] about ሕገወጥ መሣሪያዎችና ተሠርቀው የተከማቹ የመኪና ዕቃዎች ተያዙ