በባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 3 ሺህ 676 የክላሽ ጥይት፣ 1 ሺህ 288 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦችን ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ አስታውቀዋል።
እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ ገለጻ በክፍለ ከተማው ብሎም በከተማዋ መሰል ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ ተደጋግመው ቢከሰቱም በፀጥታ ኀይሉ የጠነከረ ትጋትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ።
አሸባሪው ህወሓት በየቦታው ህዝብን ለማጥፋት እሳት እያነደደ ባለበት በዚህ ጊዜ መላው ህዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሆን ወንጀልን በመከላከል እና አካባቢን በመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር ኃላፊው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply