
ህገ ወጥና ሀሰተኛ ገንዘቦችን በሚሰበስቡ ባንኮች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠነቀቁ፡፡
የኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ መቀየርን በማስመልከት ዛሬ በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንደተናገሩት፤ ከብር ኖቶች መቀየር ጋር በተያያዘ ህገ ወጥና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰበስቡ ባንኮች መኖራቸውን መንግሥት ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ አግኝቷል፡፡
በመሆኑም አዲስ የገንዘብ የብር ኖቶች መቀየራቸውን ተከትሎ መንግሥት ህገ ወጥና ሀሰተኛ የብር ኖቶችን የሚሰባስቡ ባንኮች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
መንግሥት የባንኮችን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውዱን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ባንኮችም በተለይ አሮጌው ንዘብ በአዲሱ የመቀየር ሥራ ሲሰራ ሀሰተኛና ህገ ወጥ ገንዘቦችን ከመሰብሰብ በመቆጠብ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ይህን ሀላፊነታቸው በማይወጡና ህገ ወጥ ድርጊት በሚፈጸሙ ባንኮች ላይ መንግሥት ህልውናቸውን እስከማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ያስጠነቀቁት፡፡
በአሁኑ ወቅት የአዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት እንደሚገኝና የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ገንዘቧን የሚወክል ምልክት እንዳልነበራት ይታወቃል። በቅርቡ ለብር ለያ የሚሆን አዲስ ምልክት ተዘጋጅቶ በጥቅም ላይ እንደሚውልም ተገልጿል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
That is great