
ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማኅበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል።
በሥነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል። (አል አይን)
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።
መዝገበ ቃላቱን ለማዘጋጀት አራት ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የሚዘጋጀው መዝገበ ቃላት በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች የአገሪቱ ቋንቋዎች የሚዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል።
የኦሮሞ አክራሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የአማራ ብቻ በማድረግ በጨቋኝነት ከማየት ጀምሮ እንዲጠፋ ብዙ ሲናገሩ ተደምጠዋል። በወንጀል ተከስሶ አሁን በእስር ላይ የሚገኘው በቀለ ገርባ በወለጋ ሰዎች ኦሮምኛ ካልተናገሩ ዕቃ አትሽጡላቸው ሲል መደመጡ ይታወሳል።
ሽመልስ አብዲሣ ደግሞ “ብዙ ሰርተናል፣ ብዙ ነው ማለት ነው፣ የምንችለው convince አድርገን፣ ያልቻልነውን confuse አድርገን” በሚለው የወረደ ንግግሩ “አማርኛ እየሞተ ነው የመጣው፣ ወደታች ነው እየሄደ ያለው” ማለቱ የሚታወስ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply