ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማኅበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል። በሥነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል። (አል አይን) ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።መዝገበ … [Read more...] about አማርኛ ቋንቋ በቻይና መሰጠት ተጀመረ፤ የመጀመሪያው የሕግ መዝገበቃላት በአማርኛ ሊዘጋጅ ነው